“በዚያ ዘመን ሰዎች ዳግመኛ፣ “ ‘አባቶች በበሉት ጐምዛዛ የወይን ፍሬ፣ የልጆች ጥርስ ጠረሰ’ የሚለውን ምሳሌ አይናገሩም።
እናንተ፣ ‘እግዚአብሔር የሰውን ቅጣት ለልጆቹ ያከማቻል’ ትላላችሁ፤ ነገር ግን ያውቀው ዘንድ ለሰውየው ለራሱ ይክፈለው፤
ነገር ግን፣ እያንዳንዱ በገዛ ኀጢአቱ ይሞታል፤ ጐምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሰው ሁሉ የራሱን ጥርስ ይጠርሳል።
አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው ዐለፉ፤ እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።
አባቶች በልጆቻቸው፣ ልጆችም በአባቶቻቸው አይገደሉ፤ እያንዳንዱ በራሱ ኀጢአት ይገደል።