ካህናቱን አትረፍርፌ እባርካለሁ፤ ሕዝቤም በልግስናዬ ይጠግባል፤” ይላል እግዚአብሔር።
“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ተነሥ፣ ከኀይልህ ታቦት ጋራ ወደ ማረፊያ ቦታህ ግባ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ካህናትህ ድነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በቸርነትህ ደስ ይበላቸው።
የእስራኤል ሕዝብና ሌዋውያኑ ጭምር፣ ከእህሉ፣ ከአዲሱ ወይን ጠጅና ከዘይቱ ያዋጡትን፣ የመቅደሱ ዕቃዎች ወደሚቀመጡባቸው፣ አገልጋይ ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና መዘምራኑ ወደሚያርፉባቸው ዕቃ ቤቶች ያምጡ። “እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።”
እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቷልና፤ የተራበችውንም ነፍስ በበጎ ነገር አጥግቧል።
ለካህናቷ ድነትን አለብሳለሁ፤ ቅዱሳኗም በደስታ ይዘምራሉ።
ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”
እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ስነቃም ክብርህን አይቼ እረካለሁ።
ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ።
ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ።
ነፍሴ በቅቤና በሥብ እንደሚረካ ሰው ትረካለች፤ አፌም በሚያዜሙ ከንፈሮች በደስታ ያወድስሃል።
በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።
ብፁዕ ነው፤ አንተ የመረጥኸው፣ ወደ ራስህ ያቀረብኸው፣ በአደባባይህም ያኖርኸው፤ ከተቀደሰው መቅደስህ፣ ከቤትህም በረከት እንረካለን።
ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤ ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል።
በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን።
እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋራ ሰብስቤአለሁ፤ የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤ ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ። ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንተ ፍቅረኞች ሆይ፤ እስክትረኩ ጠጡ።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣ የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።
እናንተም የእግዚአብሔር ካህናት ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤ የአምላካችን ባሮች ትባላላችሁ፤ የመንግሥታትን ሀብት ትመገባላችሁ፤ በብልጽግናቸውም ትኰራላችሁ።
የዛለችውን ነፍስ ዐድሳለሁ፤ የደከመችውንም አበረታለሁ።”
ይህች ከተማ፣ ለርሷ ያደረግሁትን በጎ ነገር ሁሉ በሚሰሙት የምድር ሕዝቦች ሁሉ ፊት ለዝና፣ ለደስታ፣ ለምስጋናና ለክብር ትሆናለች፤ ከምሰጣትም የተትረፈረፈ ብልጽግናና ሰላም የተነሣ ይፈራሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።’
እስራኤልንም ወደ መሰማሪያው እመልሰዋለሁ፤ በቀርሜሎስና በባሳን ላይ ይሰማራል፤ በኤፍሬም ተራሮችና በገለዓድም ላይ፣ እስኪጠግብ ይመገባል።
በመልካሙ ስፍራ አሰማራቸዋለሁ፤ የእስራኤል ተራሮች ከፍታም የግጦሽ መሬት ይሆናቸዋል። በመልካሙ ግጦሽ መሬት ላይ ይተኛሉ፤ እዚያም በእስራኤል ተራሮች ለምለም መስክ ላይ ይመገባሉ።
በጐተራ የቀረ ዘር አሁንም ይገኛልን? የወይኑና የበለሱ ዛፍ፣ የሮማኑና የወይራው ዛፍ እስካሁን አላፈሩም። “ ‘ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ።’ ”
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና።
በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤
እስከ እግዚአብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ፣ ከመታወቅ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር ታውቁም ዘንድ ነው።
ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በእግዚአብሔር ሞገስ ረክቷል፤ በበረከቱም ተሞልቷል፤ ባሕሩንና የደቡብን ምድር ይወርሳል።”
እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።
ለአምላካችንም መንግሥትና ካህናት አድርገሃቸዋል፤ እነርሱም በምድር ላይ ይነግሣሉ።”