Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኤርምያስ 30:5

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቷል፤ ሰላምም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያ ቀን እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኹበታል፤ ማንም ወደ ምድር ቢመለከት፣ ጨለማንና መከራን ያያል፤ ብርሃን እንኳ በደመናዎች ይጋረዳል።

ሁላችን እንደ ድቦች እናላዝናለን፤ እንደ ርግቦችም በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትሕን ፈለግን፤ ግን አላገኘንም፤ ትድግናን ፈለግን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቋል።

በምድረ በዳ ባሉት ወና ኰረብቶች ላይ፣ አጥፊዎች ይሰማራሉ፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍ፣ አንዳች ሳያስቀር ይበላል፤ የሚተርፍም የለም።

እግዚአብሔር ማሰማሪያቸውን አጥፍቷልና፣ የእረኞችን ጩኸት፣ የመንጋ ጠባቂዎችን ዋይታ ስሙ።

እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

ነገር ግን ይህ የማየው ምንድን ነው? እጅግ ፈርተዋል፤ ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ነው፤ ብርቱ ጦረኞቻቸው ተሸንፈዋል፤ ዘወር ብለውም ሳያዩ፣ በፍጥነት እየሸሹ ነው፤ በየቦታውም ሽብር አለ፣” ይላል እግዚአብሔር።

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰራዊት፣ ከሰሜን ምድር እየመጣ ነው፤ ከምድር ዳርቻም፣ ታላቅ ሕዝብ እየተነሣሣ ነው።

የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ ምርር ብለሽ አልቅሺ፤ አጥፊው በድንገት፣ በላያችን ይመጣልና።

የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣ ከዳን ይሰማል፤ በድንጉላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣ መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሊውጡ መጡ።

እንዲህ የሚለውን የሕዝቤን ጩኸት፣ ከሩቅ ምድር ስማ፤ “እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ንጉሧስ በዚያ አይኖርምን?” “በተቀረጹ ምስሎቻቸው፣ እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ለምን አስቈጡኝ?”

እነሆ የዋይታ ድምፅ ከጽዮን ተሰምቷል፤ እንዲህም ይላል፤ ‘ምንኛ ወደቅን! ውርደታችንስ እንዴት ታላቅ ነው! ቤቶቻችን ፈራርሰዋልና፤ አገራችንን ጥለን እንሂድ።’ ”

ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣ ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣ ጠጕራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤ ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።”

ነገሥታትን ይንቃል፤ በገዦችም ላይ ያፌዛል፤ በምሽግ ሁሉ ላይ ይሥቃል፤ የዐፈር ቍልል ሠርቶም ይይዘዋል።

የራሳቸው ያልሆኑትን መኖሪያ ስፍራዎች ለመያዝ፣ ምድርን ሁሉ የሚወርሩትን፣ ጨካኝና ፈጣን የሆኑትን፣ ባቢሎናውያንን አስነሣለሁ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች