Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኤርምያስ 3:6

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር በንጉሥ ኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፤ “ከዳተኛዪቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ከፍ ወዳለው ኰረብታ ሁሉ ወጥታ፣ ወደ ለመለመው ዛፍ ሥር ሁሉ ሄዳ በዚያ አመነዘረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም በእያንዳንዱ ኰረብታና በየትልልቁ ዛፍ ጥላ ሥር የማምለኪያ ኰረብቶችን አዕማደ ጣዖታት፣ የአሼራን ምስል ዐምድ ለራሳቸው አቆሙ።

ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ።

በተግባራቸው ረከሱ፤ በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ።

“እናንተ የአስማተኛዪቱ ልጆች ግን፣ እናንተ የአመንዝራውና የጋለሞታዪቱ ዘር፤ እናንተ፣ ወዲህ ኑ!

ዐልጋሽን ከፍ ባለውና በረጅሙ ኰረብታ ላይ አነጠፍሽ፤ በዚያም መሥዋዕትሽን ልታቀርቢ ወጣሽ።

የእግዚአብሔር ቃል የይሁዳ ንጉሥ፣ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ወደ ኤርምያስ መጣ፤

ቃሌን መስማት ወዳልፈለጉት ወደ ቀድሞ አባቶቻቸው ኀጢአት ተመለሱ፤ ሊያገለግሏቸውም ሌሎችን አማልክት ተከተሉ። የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋራ የገባሁትን ኪዳን አፈረሱ።

ልጆቻቸው እንኳ ሳይቀሩ፣ በለመለሙ ዛፎች ሥር፣ ከፍ ባሉ ኰረብቶችም ላይ ያሉትን፣ መሠዊያቸውንና አሼራ የተባለችውን ጣዖት ምስል ያስባሉ።

ለከዳተኛዪቱ እስራኤል ስለ ምንዝርናዋ ሁሉ የፍች ወረቀቷን ሰጥቼ አባረርኋት። ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አይታ እንዳልፈራች አየሁ፤ ወጥታም አመነዘረች።

አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ይፈጥራል፤ ሴት በወንድ ላይ ከበባ ታደርጋለች።”

የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት፣ ፈጽመው ከድተውኛል፤” ይላል እግዚአብሔር።

እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብ ብለው ለማድመጥም አልፈለጉም፤ ይልቁን የክፉ ልባቸውን ሐሳብ በእልኸኝነት ተከተሉ፤ ወደ ፊት በመሄድ ፈንታም ወደ ኋላቸው ተመለሱ።

በየመንገዱ መጠምዘዣ ላይ ጕብታሽን ባበጀሽና በየአደባባዩም መስገጃ ኰረብታ በሠራሽ ጊዜ እንደ ማንኛውም ዝሙት ዐዳሪ አልነበርሽም፤ ምክንያቱም ዋጋ አላስከፈልሽም።

“ ‘አንቺ አመንዝራ ሆይ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!

ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር ባስገባኋቸው ጊዜ፣ ከፍ ያለውን ኰረብታ ሁሉና የለመለመውን ዛፍ ሁሉ ተመለከቱ፤ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ፤ ቍርባናቸውን በማቅረብ ቍጣዬን አነሣሡ፤ መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣናቸውን ዐጠኑ፤ የመጠጥ ቍርባናቸውንም አፈሰሱ።

“እኅቷ ኦሖሊባ ይህን አይታ ነበር፤ ሆኖም በፍትወቷና በዘማዊነቷ ከእኅቷ የባሰች ብልሹ ሆነች።

የታላቂቱ ስም ኦሖላ፣ የእኅቷም ኦሖሊባ ነበር፤ ሁለቱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውም፣ ኦሖላ ሰማርያ ናት፤ ኦሖሊባም ኢየሩሳሌም።

ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤ ወደ ልዑል ቢጣሩም፣ በምንም ዐይነት አያከብራቸውም።

በተራሮችም ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፤ መልካም ጥላ ባለው፣ በወርካ፣ በኮምቦልና በአሆማ ዛፍ ሥር፣ በኰረብቶችም ላይ የሚቃጠል ቍርባን ያቀርባሉ። ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን፣ ምራቶቻችሁም አመንዝራዎች ይሆናሉ።

እስራኤላውያን ግን ሌሎችን አማልክት ተከትለው አመነዘሩ፤ ሰገዱላቸውም እንጂ መሳፍንታቸውን አልሰሙም። አባቶቻቸው እግዚአብሔርን በመታዘዝ በሄዱበት መንገድ ሳይሆን፣ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሕግ በመከተል ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች