የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህች ከተማ ስለ ቀሩት ዐምዶች፣ ከናስ ስለ ተሠራው ትልቁ ገንዳ፣ ስለ ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎችና ስለ ሌሎቹም ዕቃዎች እንዲህ ይላልና፤
ቅርጹ ክብ፣ ስፋቱ ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት ክንድ የሆነ ክብ ገንዳ ከቀለጠ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ ሆነ።
እንዲሁም ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ዐሥር ባለመንኰራኵር የዕቃ ማስቀመጫዎች ከመዳብ ሠራ፤ የእያንዳንዱም ርዝመት አራት ክንድ፣ ወርድ አራት ክንድ፣ ቁመትም ሦስት ክንድ ነበር።
ባቢሎናውያን የናስ ዐምዶቹን፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የነበሩትን ተንቀሳቃሽ የዕቃ ማስቀመጫዎችንና ከናስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ሰባበሩ፤ ናሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
እያንዳንዱም ዐምድ ከፍታው ዐሥራ ስምንት ክንድ ሲሆን፣ የናስ ጕልላት ነበረው፤ የጕልላቱ ርዝመት ሦስት ክንድ ሆኖ፣ ዙሪያውን በሙሉ የናስ መርበብና የሮማን ፍሬዎች ቅርጽ ነበረው፤ ሌላውም ዐምድ ከነቅርጾቹ ከዚሁ ጋራ ተመሳሳይ ነበር።
እርሱም ትልልቁንም ሆነ ትንንሹን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃ በሙሉ፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሀብት፣ የንጉሡንና የሹማምቱን ሀብት ሁሉ ወደ ባቢሎን አጋዘ።
ዮድ በሀብቷ ሁሉ ላይ፣ ጠላት እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ የከለከልሃቸው፣ ጣዖት የሚያመልኩ አሕዛብ፣ ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።
ጌታም የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ካሉት ዕቃዎች ከጥቂቶቹ ጋራ በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ ወደ አምላኩ ቤት ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ በአምላኩም ግምጃ ቤት ውስጥ አኖራቸው።