ስለዚህ ለነቢዩ፣ ‘እግዚአብሔር ምን መልስ ሰጠህ?’ ወይም፣ ‘እግዚአብሔር ምን ተናገረህ?’ ትለዋለህ፤
ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ ማዳኑ ለሚፈሩት በርግጥ ቅርብ ነው።
ከእንግዲህ ግን፣ ‘የእግዚአብሔር ሸክም’ ብላችሁ መናገር አይገባችሁም፤ ምክንያቱም ለሰው ሁሉ የገዛ ራሱ ቃል ሸክሙ ስለሚሆን፣ የአምላካችንን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን፣ የሕያው አምላክን ቃል ታጣምማላችሁ።
‘የእግዚአብሔር ሸክም’ ብትሉ እንኳ፣ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ፣ “የእግዚአብሔር ሸክም” አትበሉ’ ብዬ ብነግራችሁም፣ እናንተ፣ ‘የእግዚአብሔር ሸክም’ ብላችኋል፤