እግዚአብሔር የልቡን ሐሳብ፣ ሙሉ በሙሉ ሳይፈጽም፣ ቍጣው እንዲሁ አይመለስም፤ በኋለኛው ዘመን፣ ይህን በግልጽ ትረዳላችሁ።
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባችሁ እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ፤
በተጋዙበት አገር ሳሉ ወደ ልቡናቸው ቢመለሱ፣ ንስሓ ቢገቡና በምርኮ ምድር ሳሉ፣ ‘ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል’ ብለው ቢለምኑህ፣
ይህም ሆኖ እንኳ ለቍጣ እንዲነሣሣ ምናሴ ካደረጋቸው ነገሮች ሁሉ የተነሣ፣ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ከነደደው ከአስፈሪው ቍጣው ገና አልበረደም ነበር።
ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “እስራኤልን እንዳስወገድሁ ሁሉ ይሁዳንም ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኋትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና፣ ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’ ብዬ የተናገርሁለትን ይህን ቤተ መቅደስ እተዋለሁ” አለ።
እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣ አንዳችም ጥበብ፣ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሏል፤ “እንደ ዐቀድሁት በርግጥ ይከናወናል፤ እንደ አሰብሁትም ይሆናል።
ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።
የልቡን ሐሳብ ሳይፈጽም፣ የእግዚአብሔር ቍጣ፣ እንዲሁ አይመለስም፤ በሚመጡትም ዘመናት፣ ይህን ታስተውላላችሁ።
ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማያትም በላይ ይጨልማሉ፤ ተናግሬአለሁ፤ ሐሳቤን አልለውጥም፤ ወስኛለሁ፤ ወደ ኋላም አልልም።”
በባቢሎን ቅጥር ላይ ዐላማ አንሡ ጥበቃውን አጠናክሩ፤ ዘብ ጠባቂዎችን አቁሙ፤ ደፈጣ ተዋጊዎችን አዘጋጁ እግዚአብሔር በባቢሎን ሕዝብ ላይ የወሰነውን፣ ዐላማውን ያከናውናል።
የተሳለው ሊገድል፣ የተወለወለውም እንደ መብረቅ ሊብረቀረቅ ነው! “ ‘ታዲያ፣ እንዴት ደስ ሊለን ይችላል? ሰይፉ የልጄን በትረ መንግሥት እንደ ማንኛውም በትር ንቋል።
ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝሁት እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ሕዝቡ ሁሉ ያውቃል፤ እርሱም ወደ ሰገባው አይመለስም።’
ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? “እነርሱም ንስሓ ገብተው እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፣ ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።’ ”
ስትጨነቅና ይህ ሁሉ ነገር ሲደርስብህ ያን ጊዜ፣ በኋለኞቹ ዘመናት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ትመለሳለህ፤ ትታዘዝለታለህም።