Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኤርምያስ 21:10

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህች ከተማ ላይ በጎ ሳይሆን ክፉ ለማድረግ ወስኛለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ ለባቢሎን ንጉሥ ትሰጣለች፤ እርሱም በእሳት ያጠፋታል።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በእሳት አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች አፈረሱ፤ ቤተ መንግሥቶቹን በሙሉ አቃጠሉ፤ በዚያ የነበረውንም የከበረ ዕቃ በሙሉ አጠፉ።

የእግዚአብሔር ፊት ግን፣ መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።

ነገር ግን የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ ምሽጎቿን የሚበላ፣ የማይጠፋ እሳት እጭራለሁ።’ ”

ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርጋለሁ፤ ይህችንም ከተማ በምድር ሕዝብ ሁሉ ፊት የተረገመች አደርጋታለሁ።’ ”

‘ከለዳውያን በቍጣዬና በመዓቴ በምገድላቸው ሰዎች ሬሳ ይሞላሉ፤ ስለ ክፋቷ ሁሉ ከዚህች ከተማ ፊቴን እሰውራለሁ።

“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ ሄደህ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ ልሰጣት ነው፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፤

እነሆ፤ አዝዛቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደዚህችም ከተማ እንደ ገና እመልሳቸዋለሁ። እነርሱም ይወጓታል፤ ይይዟታል፤ በእሳትም ያቃጥሏታል። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባቸው፣ ባድማ አደርጋቸዋለሁ።’ ”

ኤርምያስም ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ብትሰጥ፣ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ አትቃጠልም፤ አንተና ቤተ ሰብህም በሕይወት ትኖራላችሁ።

ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ባትሰጥ ግን ይህች ከተማ ለባቢሎናውያን ዐልፋ ትሰጣለች፤ እነርሱም ያቃጥሏታል፤ አንተም ራስህ ከእጃቸው አታመልጥም።’ ”

“ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ተወስደው ለባቢሎናውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ራስህ በባቢሎን ንጉሥ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”

እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፤ ‘ይህች ከተማ በርግጥ ለባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ዐልፋ ትሰጣለች፤ እርሱም ይይዛታል።’ ”

“ሂድና ለኢትዮጵያዊው አቢሜሌክ እንዲህ በለው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ዕድገት ሳይሆን ጥፋት በማምጣት በዚህች ከተማ ላይ ቃሌን እፈጽማለሁ፤ በዚያ ጊዜ በዐይንህ እያየህ ይህ ይፈጸማል።

ባቢሎናውያን ቤተ መንግሥቱንና የሕዝቡን ቤት በእሳት አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ።

“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣትና ይሁዳን ሁሉ ለመደምሰስ ቈርጬ ተነሥቻለሁ።

ለመልካም ሳይሆን ለክፉ እተጋባቸዋለሁና፤ በግብጽ የሚኖሩ አይሁድ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ይደመሰሳሉ።

የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ ቤተ መንግሥቱን እንዲሁም በኢየሩሳሌም የሚገኙትን ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ እያንዳንዱንም ትልልቅ ሕንጻዎችንም በእሳት አወደመ።

ፊቴን በክፋት ወደ እነርሱ እመልሳለሁ፤ ከእሳት ቢያመልጡም፣ ገና እሳት ይበላቸዋል። ፊቴን በክፋት ወደ እነርሱ በመለስሁ ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

ጕድፉ እንዲቀልጥ፣ ዝገቱም በእሳት እንዲበላ፣ ባዶው ድስት እስኪሞቅ፣ መደቡም እስኪግል ከሰል ላይ ጣደው።

“ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ፤

በጠላቶቻችሁ ድል እንድትሆኑ ፊቴን በእናንተ ላይ አከብድባችኋለሁ፤ የሚጠሏችሁ ይገዟችኋል፤ ማንም ሳያሳድዳችሁም ትሸሻላችሁ።

የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣ በይሁዳ ላይ እሳት እሰድዳለሁ።”

በጠላቶቻቸው ተነድተው ለምርኮ ቢወሰዱም፣ በዚያ እንዲገድላቸው ሰይፍን አዝዛለሁ። “ለመልካም ሳይሆን ለክፉ፣ ዐይኔን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ።”

ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? “እነርሱም ንስሓ ገብተው እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፣ ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።’ ”




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች