በምድሪቱ ዝናብ ስለሌለ፣ መሬቱ ተሰነጣጥቋል፤ ገበሬዎችም ዐፍረው፣ ራሳቸውን ተከናንበዋል።
የታመንሽባቸውን እግዚአብሔር ስላዋረደ፣ በእነርሱም ስለማይከናወንልሽ፣ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያም ትወጫለሽ።
ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፤ ኋለኛው ዝናብም ጠፋ። አንቺ ግን አሁንም የጋለሞታ ገጽታ አለብሽ፤ ዐይንሽን በዕፍረት አልሰብር ብለሻል።
እናንተ ገበሬዎች፣ ዕዘኑ፤ እናንተ የወይን ገበሬዎች፣ ዋይ በሉ፤ ስለ ገብሱና ስለ ስንዴው አልቅሱ፤ የዕርሻው መከር ጠፍቷልና።
ዘሩ በዐፈር ውስጥ፣ በስብሶ ቀርቷል፤ ግምጃ ቤቶቹ ፈራርሰዋል፤ ጐተራዎቹም ተሰባብረዋል፤ እህሉ ደርቋልና።
“ ‘ከዚህ ሁሉ በኋላ ባትታዘዙኝ፣ ስለ ኀጢአታችሁ ሰባት ዕጥፍ እቀጣችኋለሁ፤
ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣ ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።
ምድሪቱ በሙሉ የተቃጠለ ጨውና ዲን ዐመድ ትሆናለች። አንዳች ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አያቈጠቍጥባትም፤ የሚያድግ ተክል አይገኝባትም። የሚደርስባት ውድመት እግዚአብሔር በታላቅ ቍጣ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፣ እንደ አዳማና ስቦይ ጥፋት ይሆናል።