ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ ነብርስ ዝንጕርጕርነቱን መለወጥ ይችላልን? እናንተ ክፉ ማድረግ የለመዳችሁትም፣ መልካም ማድረግ አትችሉም።
ነገር ግን በቀደመው ልማዳቸው ጸኑ እንጂ አልተመለሱም።
ቂልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣ እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቅቀው፣ ቂልነቱን ልታስወግድለት አትችልም።
የተጣመመው ሊቃና አይችልም፤ የሌለም ነገር ሊቈጠር አይችልም።
ለምን ዳግመኛ ትመታላችሁ? ለምንስ በዐመፅ ትጸናላችሁ? ራሳችሁ በሙሉ ታምሟል፤ ልባችሁ ሁሉ ታውኳል።
የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነው፤ ፈውስም የለውም፤ ማንስ ሊረዳው ይችላል?
በልዩ ቅጠል ብትታጠቢ፣ ብዙ ሳሙና ብትጠቀሚም፣ የበደልሽ ዕድፍ አሁንም በፊቴ ነው፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“ልጆቻችሁን በከንቱ ቀጣኋቸው፤ እነርሱም አልታረሙም። ሰይፋችሁ እንደ ተራበ አንበሳ ነቢያታችሁን በልቷል።
“ሕዝቤ ቂሎች ናቸው፤ እኔን አያውቁኝም። ማስተዋል የጐደላቸው፣ መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው። ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፣ መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”
እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን? አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።
ባልንጀራ ባልንጀራውን ያታልላል፤ እውነትን የሚናገር የለም፤ ሐሰትን ይናገሩ ዘንድ ምላሳቸውን አሠልጥነዋል፤ ኀጢአትንም በማድረግ ራሳቸውን አድክመዋል።
ሳኦልም ይህ በተነገረው ጊዜ ሌሎች ሰዎች ላከ፤ እነርሱም ትንቢት ተናገሩ፤ ሳኦል ለሦስተኛ ጊዜ ሰዎች ላከ፣ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።