ርስቴ ሌሎች አሞሮች ሊበሏት እንደ ከበቧት፣ እንደ ዝንጕርጕር አሞራ አልሆነችምን? ሂዱ፤ የዱር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፤ እንዲቀራመቷትም አምጧቸው።
እግዚአብሔርም በኢዮአቄም ላይ ባቢሎናውያን፣ ሶርያውያን፣ ሞዓባውያንና አሞናውያን አደጋ ጣዮችን ላከበት፤ በአገልጋዮቹ በነቢያቱ አማካይነት በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ይሁዳን ያጠፉ ዘንድ እነዚህን ላከ።
የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣ የተኵራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።
እናንተ የምድር አራዊት ሁሉ ኑ፤ እናንተ የዱር አራዊት ሁሉ ኑና በጥርሳቸሁ ቦጫጭቁ!
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አራት ዐይነት አጥፊዎችን እሰድድባቸዋለሁ፤ እነዚህም፣ ለመግደል ሰይፍ፣ ለመጐተት ውሾች፣ እንዲሁም ጠራርጎ ለመብላትና ለማጥፋት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ናቸው።
አንበሶች በርሱ ላይ አገሡ፤ በኀይለኛ ድምፅም ጮኹበት። ምድሩን ባድማ አድርገውበታል፤ ከተሞቹ ተቃጥለዋል፤ ወናም ሆነዋል።
ነፍሳቸውን ለሚሹ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ የሚያባርራቸውም አይኖርም።
ጽዮን እጆቿን ዘረጋች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ ጎረቤቶቹ ጠላቶቹ እንዲሆኑ፣ እግዚአብሔር በያዕቆብ ላይ ትእዛዝ አውጥቷል፤ ኢየሩሳሌምም በመካከላቸው፣ እንደ ርኩስ ነገር ተቈጠረች።
ስለዚህ እረኛ የለምና ተበተኑ፤ በመበተናቸውም ለአራዊቱ ሁሉ መብል ሆኑ።
አውሬውና ያየሃቸው ዐሥሩ ቀንዶች አመንዝራዪቱን ይጠሏታል፤ ባዶዋንና ዕራቍቷን ያስቀሯታል። ሥጋዋን ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።