በብርና በወርቅ ይለብጡታል፤ እንዳይወድቅም፣ በመዶሻ መትተው በምስማር ያጣብቁታል።
የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ ያበጃቸው፣ ብርና ወርቅ ናቸው።
የአሕዛብ ጣዖታት ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣ የሰው እጅ ያበጃቸው ናቸው።
የብረት የእጅ ጥበብ ባለሙያ መሥሪያን ይይዛል፤ በከሰል ፍም ላይ ይሠራዋል፤ ጣዖትን በመዶሻ ቅርጽ ይሰጠዋል፤ በክንዱም ኀይል ያበጀዋል። ከዚያም ይራባል፤ ጕልበት ያጣል፤ ውሃ ይጠማል፤ ይደክማል።
ሰዎች ወርቅ ከከረጢታቸው ይዘረግፋሉ፤ ብርንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ አንጥረኛን ይቀጥራሉ፤ እርሱም አምላክ አድርጎ ያበጅላቸዋል። እነርሱም ይሰግዱለታል፤ ያመልኩታልም።
አንሥተው በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ እቦታው ያደርጉታል፤ በዚያም ይቆማል፤ ከዚያም ቦታ አይንቀሳቀስም፤ ማንም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይመልስም፤ ከጭንቀቱም አያድነውም።
አሁንም ኀጢአትን መሥራት አበዙ፤ ብራቸውን አቅልጠው ለራሳቸው ጣዖት ሠሩ፣ በጥበብ የተሠሩ ምስሎችን አበጁ፤ ሁሉም የእጅ ጥበብ ባለሙያ ናቸው። ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ተብሏል፤ “ሰውን መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ፤ የጥጃ ጣዖቶችንም ይስማሉ!”
ዕንጨቱን፣ ‘ንቃ!’ ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ፣ ‘ተነሣ!’ ለሚል ወዮለት! በውኑ ማስተማር ይችላልን? እነሆ፤ በወርቅና በብር ተለብጧል፤ እስትንፋስም የለውም።”