Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኤርምያስ 1:14

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ከሰሜን በምድሪቱ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ድንገት መዓት ይወርድባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በር ሆይ፤ ዋይ በል! ከተማ ሆይ፤ ጩኽ! ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ ሁላችሁም በፍርሀት ቅለጡ! ጢስ ከሰሜን መጥቶብሃል፤ ከሰልፉ ተነጥሎ የሚቀር የለምና።

“አንዱን ከሰሜን አስነሣሁት፤ እርሱም ይመጣል፤ ከፀሓይ መውጫ የሚመጣው፣ ስሜን የሚጠራ ነው፤ ሸክላ ሠሪ ዐፈር እንደሚረግጥ፣ አለቆችን እንዲሁ እንደ ጭቃ ይረግጣል።

መርዶ ስሙ! እነሆ፤ ከሰሜን ምድር፣ ታላቅ ሽብር እየመጣ ነው፤ የይሁዳን ከተሞች ባድማ፣ የቀበሮዎችም መናኸሪያ ያደርጋል።

የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ለበኣል በማጠን ባደረጉት ክፋት ስላስቈጡኝ፣ አንቺን የተከለሽ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉ ነገር ዐውጆብሻል።

የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤

እነሆ፤ ከሰሜን ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤ በመካከላቸውም ዕውሮችና ዐንካሶች፣ ነፍሰ ጡርና በምጥ ላይ ያሉ ሴቶች ይገኛሉ፤ ታላቅም ሕዝብ ሆነው ይመለሳሉ።

ወደ ጽዮን ለመግባት ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ቶሎ ሸሽታችሁ አምልጡ፤ ከሰሜን መቅሠፍትን፣ ታላቅ ጥፋትን አመጣለሁና።”

“ግብጽ ያማረች ጊደር ናት፤ ነገር ግን ተናዳፊ ዝንብ ከሰሜን ይመጣባታል።

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፤ ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤ አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣ ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል። ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤

“እነሆ፤ ሰራዊት ከሰሜን ይመጣል፤ አንድ ኀያል መንግሥትና ብዙ ነገሥታት፣ ከምድር ዳርቻ ተነሣሥተዋል።

የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣ ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱም በርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤ መጥተውም ይይዟታል። ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣ እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።

“እናንተ የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤ በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ።

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰራዊት፣ ከሰሜን ምድር እየመጣ ነው፤ ከምድር ዳርቻም፣ ታላቅ ሕዝብ እየተነሣሣ ነው።

እኔም አየሁ፤ ስመለከትም፣ እነሆ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል መጣ፤ ይኸውም በታላቅ ብርሃን የተከበበ፣ መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበረ፤ የእሳቱም መኻል የጋለ ብረት ይመስል ነበር።

ለዚህ ዐመፀኛ ቤት እንዲህ ብለህ ተምሳሌት ተናገር፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ብረት ድስት በእሳት ላይ ጣድ፤ ከጣድህም በኋላ ውሃ ጨምርበት።

“የሰሜንን ሰራዊት ከእናንተ አርቃለሁ፤ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር በማድረግ፣ ወደ ደረቀውና ወደ ባድማው ምድር እገፋዋለሁ፤ ግማቱ ይወጣል፤ ክርፋቱም ይነሣል።” በርግጥ እርሱ ታላቅ ነገር አድርጓል።

የባለ ጥቍር ፈረሶች ወደ ሰሜን፤ የባለ ነጭ ፈረሶች ወደ ምዕራብ አገር፣ የባለዝጕርጕር ፈረሶች ወደ ደቡብ አገር ይወጣል።”




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች