እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ ዐማኑኤል ሆይ! የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።”
የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር ሊወጋው መጣ፤ ሆሴዕም ተገዛለት፤ ገበረለትም።
የተመሸጉትን የይሁዳ ከተሞች በቍጥጥሩ ሥር በማድረግ እስከ ኢየሩሳሌም ዘለቀ።
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣ በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰድደዋለሁ።
እስትንፋሱ እንደሚጠራርግ፣ እስከ ዐንገት እንደሚደርስም የውሃ ሙላት ነው፤ መንግሥታትን በጥፋት ወንፊት ያበጥራቸዋል፤ በሕዝቦችም መንጋጋ፣ መንገድ የሚያስት ልጓም ያስገባል።
በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች።
ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፣ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የሚያመጣውም የአሦርን ንጉሥ ነው።”
ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነውና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፤ ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤ አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣ ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል። ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድበታል፤ ክንፎቹንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።
ባሕር በባቢሎን ላይ ይወጣል፤ ሞገዱም እየተመመ ይሸፍናታል።
እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ትልቅ ክንፍና ረዥም ማርገብገቢያ ያለው እንዲሁም አካሉ በላባ የተሸፈነ መልኩ ዝንጕርጕር የሆነ ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጥቶ የዝግባ ዛፍ ጫፍ ያዘ፤
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የውቅያኖስንም ውሃ በላይሽ አድርጌ በቀላይ ስሸፍንሽ፣
ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እስከ ጠላት ምሽግ ደርሶ የሚዋጋና ሊቋቋሙት እንደማይቻል ጐርፍ የሚጠራርግ ታላቅ ሰራዊት ያሰባስባሉ።
ቍስሏ የማይሽር ነውና፤ ለይሁዳ ተርፏል፤ እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሷል።
እርሱም ሰላማቸው ይሆናል። አሦራዊ ምድራችንን ሲወርር፣ ምሽጎቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ ሰባት እረኞችን፣ እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።
“እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ” ማለት ነው።