እግዚአብሔር ብርቱ እጁን በላዬ አድርጎ የእነዚህን ሰዎች መንገድ እንዳልከተል አስጠነቀቀኝ፤ እንዲህም አለኝ፤
የእግዚአብሔርም ኀይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን ከፍ አድርጎ በቀበቶው ካጠበቀ በኋላ፣ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ አክዓብን ቀድሞት ሮጠ።
አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ እመክርሃለሁ፤ በዐይኔም እከታተልሃለሁ።
ልጄ ሆይ፤ ዐብረሃቸው አትሂድ፤ በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤
“ለዐመፀኞች ልጆች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእኔ ያልሆነውን ሐሳብ ይከተላሉ፤ ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ በኀጢአት ላይ ኀጢአት ይጨምራሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብትመለስ፣ መልሼ አቆምሃለሁ፤ ታገለግለኛለህም፤ የከበረውን ከማይረባው ለይተህ ብትናገር፣ አፍ ትሆነኛለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ፣ አንተ ወደ እነርሱ አትመለስም፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤ አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤ ሁሉም ተዘባበቱብኝ።
ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የርሱን ስም አላነሣም፤ በስሙም አልናገርም” ብል፣ ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም።
መንፈስ ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ወሰደኝ፤ እኔም በምሬትና በመንፈሴ ቍጣ ሄድሁ፤ የእግዚአብሔርም ጽኑ እጅ በላዬ ነበረች።
እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ወደ ኋላ አንልም።”