“ከማማጧ በፊት፣ ትወልዳለች፤ በምጥ ጣር ከመያዟ በፊት፣ ወንድ ልጅ ትገላገላለች።
እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፤ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የተግሣጽና የውርደት ቀን ነው፤ ልጆች ሊወለዱ ሲሉ ብርታት እንደሚታጣበት ቀን ሆኗል።
“አንቺ መካን፣ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፣ ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ፣ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላል እግዚአብሔር።
ሴት ቀኗ ደርሶ ስትወልድ ትጨነቃለች፤ ከተገላገለች በኋላ ግን፣ ሰው ወደ ዓለም ተወልዷልና ስለ ደስታዋ ጭንቋን ትረሳለች፤
ከላይ የሆነችው ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት ትኖራለች፤ እርሷም እናታችን ናት።