እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ አትመለስምን? ዝም ብለህ ከልክ በላይ ትቀጣናለህን?
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ?
እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ነው? የምትቈጣውስ ለዘላለም ነውን? ቅናትህስ እንደ እሳት ሲነድድ ይኖራልን?
አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤ አምላክ ሆይ፤ ጸጥ አትበል፤ ቸል አትበል።
“ለረዥም ጊዜ ዝም አልሁ፤ ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጮኻለሁ፤ ቍና ቍና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ።
ከተቀደሰው፣ ከተከበረውና ከፍ ካለው ዙፋንህ፣ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ኀይልህና ቅናትህ የት አለ? ገርነትህና ርኅራኄህ ከእኛ ርቀዋል።
“እነሆ፤ እንዲህ የሚል ተጽፎ በፊቴ ተቀምጧል፤ ዝም አልልም፤ ነገር ግን እንደ ሥራው እሰጠዋለሁ፤ የእጃቸውንም እከፍላቸዋለሁ፤
ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ፣ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በእነዚህ ሰባ ዓመታት ውስጥ የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” አለ።
እነርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ሁሉን የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ አትፈርድም? እስከ መቼስ ደማችንን በምድር በሚኖሩት ላይ አትበቀልም?” አሉ።