ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ፈጽሞ አይታክቱም። እናንተ ወደ እግዚአብሔር አቤት፣ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤
ነገር ግን፣ አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።”
በዚያ ጊዜ ሰውየው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለ ሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው።
የአባቱን የዳዊትን ሥርዐት በመከተልም፣ ካህናቱን በየአገልግሎት ክፍላቸው ሌዋውያኑንም ምስጋናውን እንዲመሩና በየዕለቱ ሥራቸው ካህናቱን እንዲረዱ መደባቸው። ደግሞም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት፣ የቤተ መቅደሱን በር ጠባቂዎች በልዩ ልዩ በሮች ጥበቃ ላይ በየክፍላቸው መደባቸው።
በቅጥርሽ ውስጥ ሰላም ይሁን፤ በምሽግሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን”።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣ ሞኝ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ ዐስብ።
ጥንት ገንዘብህ ያደረግሃትን ጉባኤ፣ የዋጀሃትን የርስትህን ነገድ፣ መኖሪያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራ ዐስብ።
በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤ እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?” አልኋቸው።
የከተማዪቱም ጠባቂዎች፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ እነዚህ የቅጥሩ ጠባቂዎች፣ ደበደቡኝ፤ አቈሰሉኝ፤ ልብሴንም ገፈፉኝ።
እስኪ ያለፈውን አስታውሰኝ፤ ተቀራርበን እንከራከርበት፤ ትክክለኛ ስለ መሆንህም አስረዳ።
እነሆ፤ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽ ምን ጊዜም በፊቴ ናቸው።
ስሚ! ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገዋል፤ በአንድነት በእልልታ ይዘምራሉ። እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ፣ በዐይኖቻቸው ያያሉ።
የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ድምፅ የለሽ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ተጋድመው ያልማሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።
ጽድቋ እንደ ማለዳ ወጋገን እስኪፈነጥቅ፣ ድነቷ እንደሚያንጸባርቅ ፋና እስኪታይ፣ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም።
ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፤ የክብርህንም ዙፋን አታዋርድ። ከእኛ ጋራ የገባኸውን ኪዳን ዐስብ፤ አታፍርሰውም።
ጠባቂዎችን አቆምሁላችሁ፤ ‘የመለከትንም ድምፅ ስሙ’ አልኋችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘አንሰማም’ አላችሁ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን ዐስብ፤ ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም።
ስለ ምን ፈጽመህ ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረዥም ጊዜ ትተወናለህ?
ከፊት የሚሄዱ ሰዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ።
እንዲህ አለኝ፤ ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ፤ ጸሎትህ ተሰምቶልሃል፤ ምጽዋትህም ለመታሰቢያነት በእግዚአብሔር ፊት ደርሷል።
ቆርኔሌዎስም በድንጋጤ ትኵር ብሎ እያየው፣ “ጌታ ሆይ፤ ምንድን ነው?” አለው። መልአኩም እንዲህ አለው፤ “ጸሎትህና ምጽዋትህ ለመታሰቢያነት ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐርጎልሃል።
እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንደኛ ሐዋርያትን፣ ሁለተኛ ነቢያትን፣ ሦስተኛ መምህራንን፣ ቀጥሎም ታምራት አድራጊዎችን፣ የመፈወስ ስጦታዎች ያላቸውን፣ ሌሎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፣ የማስተዳደር ስጦታ ያላቸውንና በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር ስጦታ ያላቸውን ሰዎች መድቧል።
ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጕዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው፤ አለዚያ አይበጃችሁም።
እነርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ሁሉን የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ አትፈርድም? እስከ መቼስ ደማችንን በምድር በሚኖሩት ላይ አትበቀልም?” አሉ።