“አዳኝ ወደ ጽዮን፣ ኀጢአታቸውንም ወደ ተናዘዙት ወደ ያዕቆብ ቤት ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር።
የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፣ በመጨረሻም በምድር ላይ እንደሚቆም ዐውቃለሁ።
የተረፉት ይመለሳሉ፣ ከያዕቆብ ቤት የተረፉት ወደ ኀያሉ አምላክ ይመለሳሉ።
እስራኤል ሆይ፤ ሕዝብህ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ቢሆንም፣ ትሩፉ ብቻ ይመለሳል። ጽድቅ የሰፈነበት ጥፋት ታውጇል።
አንተ ለጽዮን የምሥራችን የምትነግር፤ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጣ፤ አንተ ለኢየሩሳሌም ብሥራት የምትነግር፣ ድምፅህን በኀይል ከፍ አድርገህ ጩኽ። ከፍ አድርገው፤ አትፍራ፤ ለይሁዳም ከተሞች፣ “እነሆ፤ አምላካችሁ!” በል።
የመንግሥታትን ወተት ትጠጪያለሽ፤ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ፣ እንዲህ ሲል ዐውጇል፤ “ለጽዮን ሴት ልጅ፣ ‘እነሆ፤ አዳኝሽ መጥቷል! ዋጋሽ በእጁ አለ፤ ዕድል ፈንታሽም ከርሱ ጋራ ነው’ በሏት።”
በሙሴም ሕግ እንደ ተጻፈው፣ ይህ ሁሉ ጥፋት በእኛ ላይ ደረሰ፤ ሆኖም ከኀጢአታችን በመመለስና እውነትህን በመከተል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ምሕረትን አልፈለግንም፤
የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ፣ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንዳለው፣ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም፣ መድኀኒት ይገኛል፤ ከትሩፋኑም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው በዚያ ይገኛሉ።
ነገር ግን በመጀመሪያ በደማስቆ ለሚኖሩ፣ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላሉት ሁሉ፣ ከዚያም ለአሕዛብ፣ ንስሓ እንዲገቡና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ፣ የንስሓም ፍሬ እንዲያሳዩ ገልጬ ተናገርሁ።
እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤
እግዚአብሔር ብላቴናውን ባስነሣ ጊዜ፣ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ መልሶ ይባርካችሁ ዘንድ አስቀድሞ ወደ እናንተ ላከው።”
ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ለመኖር የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ለመቀደስም ፈልጉ፤ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት አይችልም።