ይህ ከሆነ ብርሃንህ እንደ ንጋት ጮራ ይፈነጥቃል፤ ፈውስህ ፈጥኖ ይደርሳል፤ ጽድቅህ ቀድሞህ ይሄዳል፤ የእግዚአብሔር ክብር ደጀን ይሆንልሃል።
ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፤ ጨለማውም እንደ ንጋት ይሆናል።
ቸር፣ ርኅሩኅና ጻድቅ እንደ መሆኑ፣ ለቅን ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል።
ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣ ፍትሕህን እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል።
ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤ ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል።
ብርሃን ለጻድቃን፣ ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።
ከዚያም ከእስራኤል ሰራዊት ፊት ፊት ሆኖ ሲሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ተመለሰና ወደ ኋላቸው መጣ፤ የደመናውም ዐምድ እንዲሁ ከፊት ተነሥቶ ከኋላቸው ቆመ፤
ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤ ጨካኝ ግን በራሱ ላይ መከራ ያመጣል።
ለጋስ ይበለጽጋል፤ ሌሎችን የሚያረካም ራሱ ይረካል።
የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።
በእምነቱ የጸና ጻድቅ የሆነ ሕዝብ ይገባ ዘንድ፣ በሮቿን ክፈቱ።
እግዚአብሔር የሕዝቡን ስብራት ሲጠግን፣ ያቈሰለውንም ሲፈውስ፣ ጨረቃ እንደ ፀሓይ ታበራለች፤ የፀሓይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት ዕጥፍ ይደምቃል።
በጽዮን ተቀምጦ፣ “ታምሜአለሁ” የሚል አይኖርም፤ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ኀጢአትም ይቅር ይባላል።
ሆኖም በችኰላ አትወጡም፤ ሸሽታችሁም አትሄዱም፤ እግዚአብሔር ፊት ፊታችሁ ይሄዳል፤ የእስራኤል አምላክ ደጀን ይሆናችኋል።
መንገዶቹን አይቻለሁ፤ ቢሆንም እፈውሰዋለሁ፤ እመራዋለሁ፤ ለርሱና ስለ እርሱ ለሚያለቅሱትም መጽናናትን እመልሳለሁ፤
“ብርሃንሽ መጥቷልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻል።
እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወጥቶልሻል፤ ክብሩንም ይገልጥልሻል።
ጽድቋ እንደ ማለዳ ወጋገን እስኪፈነጥቅ፣ ድነቷ እንደሚያንጸባርቅ ፋና እስኪታይ፣ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም።
አንተን ግን መልሼ ጤነኛ አደርግሃለሁ፤ ቍስልህንም እፈውሳለሁ፤’ ይላል እግዚአብሔር። ‘የተናቀች ማንም የማይፈልጋት ጽዮን’ ብለውሃልና።
“ ‘ይሁን እንጂ፣ ፈውስንና ጤንነትን እንደ ገና እሰጣታለሁ፤ ሕዝቤንም እፈውሳለሁ፤ በብዙ ሰላምና በርጋታ እንዲኖሩ አደርጋለሁ።
“እኔ ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ፤ እንዲሁ በፈቃደኛነት እወድዳቸዋለሁ፤ ቍጣዬ ከእነርሱ ተመልሷልና።
ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሓይ በክንፎቿ ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም እንደ ሠባ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።
የሕዝቡ ልብ ደንድኗልና፤ ጆሯቸውም አይሰማም፤ እንዳያዩም ዐይናቸውን ጨፍነዋል፤ ይህ ባይሆን ኖሮ፣ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው፣ በልባቸውም አስተውለው፣ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኋቸው ነበር።’
እንዲህ አለኝ፤ ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ፤ ጸሎትህ ተሰምቶልሃል፤ ምጽዋትህም ለመታሰቢያነት በእግዚአብሔር ፊት ደርሷል።
ነገር ግን እርሱን የሚፈሩትንና ጽድቅን የሚያደርጉትን ሁሉ ከየትኛውም ወገን ቢሆኑ ይቀበላቸዋል።
ቆርኔሌዎስም በድንጋጤ ትኵር ብሎ እያየው፣ “ጌታ ሆይ፤ ምንድን ነው?” አለው። መልአኩም እንዲህ አለው፤ “ጸሎትህና ምጽዋትህ ለመታሰቢያነት ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐርጎልሃል።