ከመዝጊያሽና ከመቃንሽ ጀርባ፣ የጣዖት ምስሎችሽን ሰቀልሽ፤ እኔን ትተሽ መኝታሽን ገላለጥሽ፤ በላይም ወጥተሽ በጣም ገለጥሽው፤ መኝታቸውን ከወደድሽላቸው ጋራ ስምምነት አደረግሽ፤ ዕርቃናቸውንም አየሽ።
“ ‘ነገር ግን በውበትሽ ተመካሽ፤ ዝናሽንም ለአመንዝራነት ተጠቀምሽበት፤ ከዐላፊ አግዳሚው ጋራ ያለ ገደብ አመነዘርሽ፣ ውበትሽም ለማንም ሆነ።
“ ‘አንቺ ከገዛ ባሏ ይልቅ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ነሽ!
በተዋበ ዐልጋ ላይ ተቀመጥሽ፤ ዕጣኔንና ዘይቴን ያኖርሽበትንም ጠረጴዛ ከዐልጋው ፊት ለፊት አደረግሽ።