ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ መጻተኛ፣ “እግዚአብሔር በርግጥ ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፣ “እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።
“ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ፣ ነገር ግን ከስምህ ታላቅነት የተነሣ ከሩቅ የመጣ ባዕድ ሰው ቢኖር፣ ሰዎች ከሩቅ የሚመጡት ስለ ታላቁ ስምህ፣ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፣ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምተው ነውና፤ መጥተው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልዩ፣
አይሁድ በታዘዘውና በተወሰነው ጊዜ እነርሱና ዘሮቻቸው፣ እነርሱን የተጠጓቸውም ሁሉ እነዚህን ሁለት ቀኖች በየዓመቱ ባለማቋረጥ እንዲያከብሩ ሥርዐት አድርገው ራሳቸው ወሰኑ።
እግዚአብሔር ለያዕቆብ ይራራለታል፤ እስራኤልን እንደ ገና ይመርጠዋል፤ በራሳቸውም አገር ያኖራቸዋል። መጻተኞች ዐብረዋቸው ይኖራሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋራ ይተባበራሉ።
ከአብራክህ ከሚከፈሉት፣ ከዘርህ፣ ከአንተ ከሚወለዱት ልጆች ተወስደው፣ በባቢሎን ንጉሥ ቤተ መንግሥት ጃንደረባዎች ይሆናሉ።”
በቤተ መቅደሴና በቅጥሮቼ ውስጥ፣ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የበለጠ፣ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘላለም፣ የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።
እርሱን ለማገልገል፣ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋራ ያቈራኙ መጻተኞች፣ የእግዚአብሔርን ስም በመውደድ፣ እርሱንም በማምለክ፣ ሰንበትን ሳያረክሱ የሚያከብሩትን ሁሉ፣ ቃል ኪዳኔንም የሚጠብቁትን፣
ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ ፊታቸውንም ወደዚያ ያቀናሉ። መጥተውም ከቶ በማይረሳ፣ በዘላለም ቃል ኪዳን፣ ከእግዚአብሔር ጋራ ይጣበቃሉ።
ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቍስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ።
እንደዚሁም በመካከላችሁ ከሚኖሩት መጻተኞችና ከተወለዱት ወገናቸው ባሪያዎችን ግዙ፤ ንብረታችሁም ይሁኑ።
እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክት ሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣ እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለርሱ ይሰግዳሉ።
እነርሱም የመገናኛውን ድንኳን ለመከባከብ ማለትም በድንኳኑ ውስጥ የሚሠራውን ሥራ ሁሉ ኀላፊነት በመውሰድ ዐብረዋችሁ ይሁኑ፤ ከዚህ በተረፈ ግን እናንተ ወዳላችሁበት ማንም ሰው አይጠጋ።
ይሁን እንጂ በመሠዊያው ላይ የሚደረገውንና በመጋረጃ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም የክህነት አገልግሎት የምትፈጽሙት አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ፤ የክህነቱን አገልግሎት ስጦታ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። ከእናንተ በቀር ወደ መቅደሱ የሚጠጋ ቢኖር ግን ይገደል።”
ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፤ “እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ በእውነት ተረድቻለሁ፤
አይሁድም አንዳንዶቹ የሰሙትን በመቀበል ከጳውሎስና ከሲላስ ጋራ ተባበሩ፤ ደግሞም ቍጥራቸው ብዙ የሆነ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ግሪኮችና አያሌ ዕውቅ ሴቶች የሰሙትን ተቀብለው ከእነርሱ ጋራ ተባበሩ።
ከዚያም ወጥቶ ቲቶስ ኢዮስጦስ ወደ ተባለ፣ እግዚአብሔርን ወደሚያመልክ ሰው ቤት ሄደ፤ የዚህም ሰው ቤት በምኵራቡ አጠገብ ነበር።
በእግዚአብሔር ወንጌል የክህነት ተግባር፣ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ለመሆን ነው፤ ይኸውም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።
ነገር ግን ከጌታ ጋራ የሚተባበር ከርሱ ጋራ አንድ መንፈስ ይሆናል።
በዚያ ዘመን ከክርስቶስ ተለይታችሁ፣ ከእስራኤል ወገንነት ርቃችሁ፣ ለኪዳኑም ተስፋ ባዕዳን ሆናችሁ፣ በዓለም ላይ ያለ ተስፋና ያለ እግዚአብሔር እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።
እናንተም ደግሞ እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ማደሪያ ትሆኑ ዘንድ ዐብራችሁ እየተገነባችሁ ነው።
ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በሰፈርህ ጊዜ፣ ከማናቸውም ርኩሰት ራስህን ጠብቅ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፤ በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በእስያና በቢታንያ ተበትነው በመጻተኛነት ለሚኖሩ ለእግዚአብሔር ምርጦች፤