የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፣ የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው!
እነርሱም ቤን ሃዳድና ከርሱ ጋራ ተባብረው የነበሩት ሠላሳ ሁለቱ ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሰክረው ሳለ እኩለ ቀን ላይ መጡ።
“ጕቦ አትቀበል፤ ጕቦ አጥርተው የሚያዩትን ሰዎች ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።
የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በእነዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም።
ዋይታ የማን ነው? ሐዘንስ የማን ነው? ጠብ የማን ነው? ብሶትስ የማን ነው? በከንቱ መቍሰል የማን ነው? የዐይን ቅላትስ የማን ነው?
“ልሙኤል ሆይ፤ ነገሥታት ይህን ማድረግ የለባቸውም፤ ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፣ ገዦችም የሚያሰክር መጠጥ ሊያስጐመጃቸው አይገባም፤
አለዚያ ጠጥተው የሕጉን ድንጋጌ ይረሳሉ፤ የተጨቈኑትን ሁሉ መብት ይገፍፋሉ።
ነገር ግን እነሆ፤ ደስታና ሐሤት፣ ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ! “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ!” አላችሁ።
ከእንግዲህ እየዘፈኑ የወይን ጠጅ አይጠጡም፤ መጠጡም ለሚጠጡት ይመርራል።
እነዚህም በወይን ጠጅ ይንገዳገዳሉ፤ በሚያሰክርም መጠጥ ይወላገዳሉ፤ ካህናቱና ነቢያቱ በሚያሰክር መጠጥ ተንገዳገዱ፤ በወይን ጠጅ ነገር ተምታታባቸው፤ በሚያሰክር መጠጥ ተወላገዱ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፤ ፍርድ ሲሰጡም ይሰናከላሉ።
የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋ ማልደው ለሚነሡ፣ እስኪያነድዳቸውም ወይን በመጠጣት ሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸው!
እርስ በርሳቸውም፣ “ኑና የወይን ጠጅ እንገባበዝ፤ እስክንሰክር እንጠጣ፤ ነገም ያው እንደ ዛሬ፣ ምናልባትም የተሻለ ቀን ይሆንልናል” ይባባላሉ።
“ኀፍረተ ሥጋቸውን ለማየት፣ ባልንጀሮቹን ለሚያጠጣ፣ እስኪሰክሩም ድረስ ለሚቀዳላቸው ወዮለት!