ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፣ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ ጨልሞም እያዩ፣ ‘ብርሃን ቀርቧል’ ይላሉ።
ከሐሰት ክስ ራቅ፤ በደል የሌለበትን ወይም ጻድቁን ሰው ለሞት አሳልፈህ አትስጥ፣ በደለኛውን ንጹሕ አላደርግምና።
በደለኛውን ማጽደቅ ሆነ፣ ጻድቁን በደለኛ ማድረግ፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።
የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤ የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
ከእንግዲህ እየዘፈኑ የወይን ጠጅ አይጠጡም፤ መጠጡም ለሚጠጡት ይመርራል።
ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፣ በተከሳሽ ላይ ወጥመድ የሚዘረጉ፣ በሐሰት ምስክር ፍትሕን ከንጹሓን የሚቀሙ ይቈረጣሉ።
ባለራእዮችን፣ “ከእንግዲህ ራእይን አትዩ!” ይላሉ፤ ነቢያትንም እንዲህ ይላሉ፤ “እውነተኛውን ትንቢት ከእንግዲህ አትንገሩን፤ ደስ የሚያሠኘውን ንገሩን፤ የሚያማልለውን ተንብዩልን።
ከእንግዲህ ሰነፍ ጨዋ አይባልም፤ ጋጠወጥም አይከበርም።
ዕፍኝ ለማይሞላ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ስትሉ ሐሰትን የሚያደምጥ ሕዝቤን እየዋሻችሁ መሞት የማይገባውን በመግደል፣ መኖር የማይገባውንም በማትረፍ በሕዝቤ መካከል አርክሳችሁኛል።
እናንተ ፍትሕን ወደ መራርነት የምትለውጡ፣ ጽድቅንም ወደ ምድር የምትጥሉ ወዮላችሁ!
መልካሙን ጠላችሁ፤ ክፉውንም ወደዳችሁ፤ የሕዝቤን ቈዳ ገፈፋችሁ፤ ሥጋቸውንም ከዐጥንቶቻቸው ለያችሁ፤
ስለዚህ ሕግ ደክሟል፤ ፍትሕ ድል አይነሣም፤ ፍትሕ ይጣመም ዘንድ፣ ክፉዎች ጻድቃንን ይከብባሉ።
እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችሁታል። እናንተም፣ “ያታከትነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ? “ክፉ የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነው፤ እርሱም በክፉዎች ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ ወዴት ነው?” በማለታችሁ ነው።
አሁን ግን ትዕቢተኞችን ቡሩካን እንላቸዋለን፤ ክፉ አድራጊዎች ይበለጽጋሉ፤ እግዚአብሔርን የሚፈታተኑትም ያመልጣሉ።’ ”
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ በሰዎች ፊት ራሳችሁን የምታጸድቁ ናችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰዎች ዘንድ የከበረ፣ በእግዚአብሔር ፊት የረከሰ ነውና።
በሰዎች መካከል ጠብ ቢነሣና ወደ ፍርድ አደባባይ ቢሄዱ፣ ዳኞች ተበዳይን ነጻ፣ በዳይን ግን ጥፋተኛ በማድረግ የፍርድ ውሳኔ ይስጡ።
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፣ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፣ ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ በዚህም በራሳቸው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣሉ።