ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ገና ድሮ ነገርሁህ፤ ከመፈጸማቸው በፊት አስታወቅሁህ፤ ይህም፣ ‘ጣዖቶቼ ይህን አደረጉ፤ ከዕንጨት የተቀረጸው ምስልና ከብረት የተሠራው አምላኬ ይህን ወስኗል’ እንዳትል ነው።
እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤
እስኪ እንደ እኔ ማን አለ? ይናገር፤ ሕዝቤን ከጥንት ስመሠርት ምን እንደ ነበረ፣ ገና ወደ ፊት ምን እንደሚሆን፣ ይናገር፤ በፊቴ ያስረዳ፤ ስለሚመጣውም ነገር አስቀድሞ ይናገር።
አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ይህን አልነገርኋችሁምን? ቀድሞስ አላሳወቅኋችሁምን? ለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አለን? ፈጽሞ! ወይም ሌላ ዐለት አለ? የለም! ማንንም አላውቅም።”
“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንተ ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።
የመጨረሻውን ከመጀመሪያው፣ ገና የሚመጣውንም ከጥንቱ ተናግሬአለሁ፤ ‘ምክሬ የጸና ነው፤ ደስ የሚያሠኘኝንም ሁሉ አደርጋለሁ’ እላለሁ።
የቀደሙትን ነገሮች ከብዙ ዘመን በፊት ተናግሬአለሁ፤ ከአፌ ወጥተዋል፤ እንዲታወቁም አድርጌአለሁ፤ እኔም ድንገት ሠራሁ፤ እነርሱም ተፈጸሙ።
ይህም ጥንት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረው፣
እነርሱም ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው።