እናንተ ልበ ደንዳኖች፣ ከጽድቅም የራቃችሁ ስሙኝ።
ደባ የሚያውጠነጥኑ ወደ እኔ ቀርበዋል፤ ከሕግህ ግን የራቁ ናቸው።
ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው።
እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤ በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ።
ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤ አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ ከኀያላኑም መካከል፣ እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም።
ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ፣ እናንተ ፌዘኞች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
አድምጡ ድምፄን ስሙ፤ አስተውሉ ቃሌንም ስሙ።
“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንተ ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።
“እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ ከተፀነሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የያዝኋችሁ፣ ከተወለዳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የተሸከምኋችሁ ስሙኝ።
“የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳ ዘር የተገኛችሁ፣ እናንተ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣ በእውነት ወይም በጽድቅ ሳይሆን፣ የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ ይህን ስሙ!
የቱን ያህል እልኸኛ እንደ ነበርህ ዐውቃለሁና፤ የዐንገትህ ጅማት ብረት፣ ግንባርህም ናስ ነበር።
የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የወይን ቦታው የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።
ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቋል፤ ጽድቅም በሩቁ ቆሟል፤ እውነት በመንገድ ላይ ተሰናክሏል፤ ቅንነትም መግባት አልቻለም።
እውነት የትም ቦታ አይገኝም፤ ከክፋት የሚርቅ ለጥቃት የተጋለጠ ነው። እግዚአብሔር ተመለከተ፤ ፍትሕ በመታጣቱም ዐዘነ።
ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።
ሕዝቡ በሙሉ፣ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፣ ከንቱ ነገርን የተከተሉት፣ ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት፣ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?
እናንተ ፍትሕን ወደ መራርነት የምትለውጡ፣ ጽድቅንም ወደ ምድር የምትጥሉ ወዮላችሁ!
ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ? እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ አለ፤ ጠብና ግጭት በዝቷል።
“እናንተ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ! ዐንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ።
አሁን ግን እናንተ ቀድሞ ርቃችሁ የነበራችሁ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም አማካይነት ቀርባችኋል።
ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።