Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኢሳይያስ 46:1

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቤል ተዋረደ፤ ናባው እጅግ ዝቅ አለ፤ ጣዖቶቻቸው በአጋሰስ ተጭነዋል፤ ይዘዋቸው የሚዞሩት ምስሎች ሸክም ናቸው፤ ለደከሙ እንስሳት ከባድ ጭነት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ?

“እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ ምድር ላይ ዐልፋለሁ፤ ከሰውም ከእንስሳም የተወለደውን የበኵር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽን አማልክት ሁሉ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።

በዚያ ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።

እነሆ፤ አንድ ሰው በፈረሶች በሚሳብ በሠረገላ መጥቷል፤ እንዲህም ሲል መለሰ፣ ‘ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች! የአማልክቷም ምስሎች ሁሉ፣ ተሰባብረው ምድር ላይ ወደቁ!’ ”

በኔጌብ ስላሉት እንስሳት የተነገረ ንግር፤ መልእክተኞች ሀብታቸውን በአህያ፣ ውድ ዕቃዎቻቸውን በግመል ጭነው፣ ተባዕትና እንስት አንበሶች፣ መርዘኛና ተወርዋሪ እባቦች በሚኖሩበት፣ መከራና ጭንቅ ባለበት ምድር ዐልፈው፣ ወደማይጠቅማቸው ወደዚያ ሕዝብ፣

“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንተ ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም።

አንሥተው በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ እቦታው ያደርጉታል፤ በዚያም ይቆማል፤ ከዚያም ቦታ አይንቀሳቀስም፤ ማንም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይመልስም፤ ከጭንቀቱም አያድነውም።

ጣዖቶቻቸው በኪያር ዕርሻ መካከል እንደ ቆመ ማስፈራርቾ ናቸው፤ የመናገር ችሎታ የላቸውም፤ መራመድም ስለማይችሉ፣ ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል፤ ጕዳት ማድረስም ሆነ፣ መልካምን ነገር ማድረግ ስለማይችሉ፣ አትፍሯቸው።”

“በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤ አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤ ‘ባቢሎን ትያዛለች፤ ቤል ይዋረዳል፤ ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤ ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤ አማልክቷም ይሸበራሉ።’

ድርቅ በውሆቿ ላይ መጣ! እነሆ፤ ይደርቃሉ፤ ምድሪቱ በፍርሀት በሚሸበሩ አማልክት፣ በጣዖትም ብዛት ተሞልታለችና።

ቤልን በባቢሎን ውስጥ እቀጣለሁ፤ የዋጠውን አስተፋዋለሁ፤ ሕዝቦች ከእንግዲህ ወደ እርሱ አይጐርፉም፤ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።

የባቢሎንን ጣዖታት የምቀጣበት ጊዜ፣ በርግጥ ይመጣልና። ምድሯ በሙሉ ትዋረዳለች፤ የታረዱትም በሙሉ በውስጧ ይወድቃሉ።

“እንግዲህ ጣዖቶቿን የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምድሯም ሁሉ፤ ቍስለኞች ያቃስታሉ።

አማልክታቸውን፣ የብረት ምስሎቻቸውን፣ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ የከበሩ ዕቃዎቻቸውን ይማርካል፤ ወደ ግብጽም ይወስዳል። ለጥቂት ዓመታትም ከሰሜኑ ንጉሥ ጋራ ከመዋጋት ይቈጠባል።

ናቡከደነፆርም እንዲህ አላቸው፤ “ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ሆይ፤ እኔ ላቆምሁት ምስል አለመስገዳችሁ፣ አማልክቴንም አለማገልገላችሁ እውነት ነው?

አንቺ ነነዌ፤ እግዚአብሔር ስለ አንቺ እንዲህ ብሎ አዝዟል፤ “ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፤ በአማልክታችሁ ቤት ያሉትን፣ የተቀረጹትን ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩትን ጣዖታት እደመስሳለሁ፤ መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፤ አንተ ክፉ ነህና።”

እንዲሁም ስማቸው የተለወጠውን ናባውን፣ በኣልሜዎንን፣ ሴባማንን ዐደሱ፤ ላደሷቸውም ከተሞች ስም አወጡላቸው።

እንዲሁም ለመሸከም የማይቻል ከባድ ሸክም አስረው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፤ ራሳቸው ግን በጣታቸው እንኳ አይነኩትም።

የአሽዶድም ሰዎች በማግስቱም ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ እነሆ፣ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት። ከዚያም አንሥተው ወደ ቦታው መለሱት።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች