ተራራውንና ኰረብታውን አፈርሳለሁ፤ ዕፀዋቱን ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዙንም ደሴት አደርጋለሁ፤ ኵሬውን አደርቃለሁ።
ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የተራሮችም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ።
“እነሆ፣ አዲስ የተሳለና ባለጥርስ ማሄጃ አደርግሃለሁ፤ ተራሮችን ታሄዳለህ፤ ታደቅቃቸዋለህ፤ ኰረብቶችንም ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
ጥልቁን ውሃ፣ ‘ደረቅ ሁን፤ ወንዞችህን አደርቃለሁ’ እላለሁ።
ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ።
በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።
ተራሮችን ተመለከትሁ፣ እነሆ ይንቀጠቀጡ ነበር፤ ኰረብቶችም ሁሉ ተናጡ።
በዚያ ጊዜ በቅናቴና በሚያስፈራው ቍጣዬ በእስራኤል ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ይሆናል ብዬ ተናግሬአለሁ።
የባሕር ዓሦች፣ የሰማይ ወፎች፣ የምድር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳብ ፍጡር ሁሉ፣ እንዲሁም በምድር ላይ ያለ ሰው ሁሉ፣ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮች ይገለባበጣሉ፤ ገደሎች ይናዳሉ፤
“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በቅርቡ፣ አንድ ጊዜ እንደ ገና ሰማያትንና ምድርን፣ ባሕሩንና የብሱን አናውጣለሁ።
በመከራ ባሕር ውስጥ ያልፋሉ፤ የባሕሩ ማዕበል ጸጥ ይላል፤ የአባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል። የአሦር ትምክሕት ይዋረዳል፤ የግብጽም በትረ መንግሥት ያበቃል።
በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማዪቱም አንድ ዐሥረኛ ወደመ፤ በነውጡም ሰባት ሺሕ ሰዎች ሞቱ፤ የተረፉትንም ፍርሀት ያዛቸው፤ ለሰማይም አምላክ ክብር ሰጡ።
ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲዘጋጅላቸው የወንዙ ውሃ ደረቀ።
ከዚያም መብረቅ፣ ድምፅ፣ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ የምድር መናወጥ ታይቶ አይታወቅም፤ ነውጡም እጅግ ታላቅ ነበር።
ከዚህ በኋላ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።