እነሆ፤ እናንተ ከምንም የማትቈጠሩ ናችሁ፤ ሥራችሁ ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ነው፤ የመረጣችሁም አስጸያፊ ነው።
እነዚህን የሚያበጁ፣ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
ሕግን ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው።
እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤ ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል።
አማልክታቸውን ወደ እሳት ጥለዋል፤ በሰው እጅ የተቀረጹ የድንጋይና የዕንጨት ምስሎች እንጂ አማልክት አልነበሩምና።
እነሆ፤ ሁሉም ከንቱ ናቸው! ሥራቸውም መና ነው፤ ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው።
“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”
ሁሉም ሰው ጅልና ዕውቀት የለሽ ነው። የወርቅ አንጥረኛው ሁሉ በሠራው ጣዖት ዐፍሯል፤ የቀረጻቸው ምስሎቹ የሐሰት ናቸው፤ እስትንፋስም የላቸውም።
እነርሱ ከንቱ የፌዝ ዕቃዎች ናቸው፤ ፍርድ ሲመጣባቸው ይጠፋሉ።
ጣዖቶቻቸው በኪያር ዕርሻ መካከል እንደ ቆመ ማስፈራርቾ ናቸው፤ የመናገር ችሎታ የላቸውም፤ መራመድም ስለማይችሉ፣ ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል፤ ጕዳት ማድረስም ሆነ፣ መልካምን ነገር ማድረግ ስለማይችሉ፣ አትፍሯቸው።”
ከከንቱ የዕንጨት ጣዖት ትምህርት የሚቀሥሙ ሁሉ፣ ጅሎችና ሞኞች ናቸው።
እንግዲህ፣ ለጣዖት የተሠዋ ሥጋ ስለ መብላት፣ በዚህ ዓለም ጣዖት ከንቱ እንደ ሆነና ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
“የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራውን፣ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ የሆነውን ምስል የሚቀርጽ ወይም ጣዖትን የሚያበጅ፣ በስውርም የሚያቆም ሰው የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።
የአማልክታቸውን ምስሎች በእሳት አቃጥል፤ በላያቸው የሚገኘውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ ለራስህ አታድርግ፤ አለዚያ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ስለ ሆነ ያሰናክልሃል።
አስጸያፊ ነገርን ወደ ቤትህ ወይም ወደ ራስህ አታምጣ፤ አለዚያ አንተም እንደ እርሱ ለጥፋት ትዳረጋለህ፤ ፈጽመህ ጥላው፤ ተጸየፈውም፤ ለጥፋት የተለየ ነውና።
በግንባሯም ላይ እንዲህ የሚል የምስጢር ስም ተጽፎ ነበር፤ ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ርኩሰቶች እናት።