ነቢዩም፣ “በቤተ መንግሥትህ ያዩት ምንድን ነው?” አለው። ሕዝቅያስም፣ “በቤተ መንግሥቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ ከንብረቴ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” አለ።
ሰዎች እንደሚያደርጉት በደሌን በልቤ በመሰወር፣ ኀጢአቴን ሸሽጌ ከሆነ፣
በሀብት ላይ ዐይንህን ብትጥል፣ ወዲያው ይጠፋል፤ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር፣ በርግጥ ክንፍ አውጥቶ ይበርራል።
ኀጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምሕረትን ያገኛል።
ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ “እነዚያ ሰዎች ምን አሉህ? ወደ አንተ ዘንድ የመጡትስ ከየት ነው?” አለው። ሕዝቅያስም፣ “ወደ እኔ የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው።
ከዚያም ኢሳይያስ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤
በአገርህ ሁሉ ከተፈጸመው ኀጢአት የተነሣ፣ በምድሪቱ ያለህ ተራራዬ፣ ሀብትህንና ንብረትህን ሁሉ፣ መስገጃ ኰረብቶችህንም ጭምር፣ ለብዝበዛ አደርገዋለሁ።
ኢያሱም አካንን፣ “ልጄ ሆይ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጥ፤ ለርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውን ሳትደብቅ ንገረኝ” አለው።
ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።