በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባልዳን ልጅ፣ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመምና መፈወስ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።
ዳዊትም፣ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ ሁሉ፣ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ወሮታውን ልክፈል” ሲል ዐሰበ። ስለዚህ ስለ አባቱ ሞት የተሰማውን ሐዘን እንዲገልጹለት ዳዊት መልክተኞችን ላከ። የዳዊት ሰዎች ወደ አሞናውያን ምድር በደረሱ ጊዜ፣
ቶዑ ከአድርአዛር ጋራ ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፣ ሰላምታና በአድርአዛር ላይ ስለ ተቀዳጀውም ድል የደስታ መግለጫ እንዲያቀርብለት፣ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።
ብዙዎችም ለእግዚአብሔር መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስም ውድ የሆኑ ገጸ በረከቶችን አመጡለት፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮም በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።
የሕዝቅያስ ልብ ግን ታበየ እንጂ ስለ ተደረገለት በጎ ነገር ተገቢ ምላሽ አልሰጠም፤ በዚህ ምክንያት የእግዚአብሔር ቍጣ በርሱ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ።
ነገር ግን በምድሪቱ ላይ ስለ ተፈጸመው ታምራዊ ምልክት እንዲጠይቁት፣ የባቢሎን ገዦች መልእክተኞችን በላኩ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሊፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ሊያውቅ ስለ ፈለገ ተወው።
የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ያየው ንግር፤
የመንግሥታት ዕንቍ፣ የከለዳውያን ትምክሕት የሆነችውን ባቢሎንን፣ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል።
በባቢሎን ንጉሥ ላይ ትሣለቃለህ፤ እንዲህም ትላለህ፤ ጨቋኙ እንዴት አበቃለት! አስገባሪነቱስ እንዴት አከተመ!
እነሆ፤ የባቢሎናውያንን ምድር ተመልከቱ፤ ሕዝቡ ከንቱ ሆኗል! አሦራውያን የምድረ በዳ አራዊት መፈንጪያ አደረጓት፤ የግንብ ማማቸውን ሠሩባት፤ ምሽጎቿን አወደሙ፤ የፍርስራሽ ክምር አደረጓት።