በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ ወደዚህች ከተማም አይገባም” ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣ አንዳችም ጥበብ፣ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።
እነዚያ ንግግራቸው የማይገባ፣ የሚሉትም የማይታወቅ፣ ሊረዱት የማይቻል ቋንቋ የሚናገሩትን ጋጠወጥ ሕዝብ ከእንግዲህ አታያቸውም።
በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣ እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፣ ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።’
“ስለ ራሴና፣ ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል፣ ይህችን ከተማ እጋርዳታለሁ፤ አድናታለሁም።”