የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም አማልክትስ የት ደረሱ? እነዚህ ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?
የሐማት ንጉሥ ቶዑ፣ ዳዊት መላውን የአድርአዛርን ሰራዊት ማሸነፉን በሰማ ጊዜ፣
የአሦርም ንጉሥ ሕዝቡን ከባቢሎን፣ ከኩታ፣ ከአዋና ከሐማት፣ ከሴፈርዋይም ከተሞች አምጥቶ በእስራኤላውያን ቦታ እንዲገቡ በሰማርያ ከተሞች አሰፈራቸው፤ እነርሱም ሰማርያን ወርሰው በከተሞቿ ይኖሩ ጀመር።
እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤ በልቡም ይህ አልነበረም፤ ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፣ ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር።
ስለ ደማስቆ፣ “ክፉ ወሬ ሰምተዋልና፣ ሐማትና አርፋድ ደንግጠዋል፤ እንደ ተናወጠ ባሕርም ታውከዋል፤ ልባቸውም ቀልጧል።
ከሖር ተራራ እስከ ሌቦ ሐማት እንደዚሁ አድርጉ፤ ከዚያም ወሰኑ እስከ ጽዳድ ይሄድና