ጕጕት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ትታቀፋቸዋለች፤ ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ።
የእባብ ዕንቍላል ታቀፉ፤ የሸረሪት ድር ዐደሩ፤ ዕንቍላሎቻቸውን የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤ አንዱ በተሰበረ ጊዜም እፉኝት ይወጣል።
ጭልፊት፣ ጭላት፣ ማንኛውም ዐይነት ዐድኖ በል አሞራ፣