እናንተ በሩቅ ያላችሁ ያደረግሁትን ስሙ፤ እናንተ በቅርብ ያላችሁ ኀይሌን ዕወቁ!
እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቷል፤ ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች። ሃሌ ሉያ።
አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ።
አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤ የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል።
እናንተ የዓለም ሕዝቦች፣ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፣ በተራሮች ላይ ምልክት ሲሰቀል ታዩታላችሁ፤ መለከትም ሲነፋ ትሰሙታላችሁ።
አሁንም እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ መሆንህን ያውቁ ዘንድ፣ አቤቱ ከእጁ አድነን።”
እናንተ ደሴቶች ስሙኝ፤ እናንተ በሩቅ ያላችሁ ሕዝቦች ይህን አድምጡ፤ በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ እግዚአብሔር ጠራኝ፤ ከመወለዴ በፊት በስም ጠራኝ።
እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣ የተቀደሰ ክንዱን ይገልጣል፤ በምድር ዳርቻዎች ያሉ ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።
በእስራኤል አልቃሾች ከንፈር ላይ ምስጋና እፈጥራለሁ። በቅርብና በሩቅ ላሉት ሰላም፣ ሰላም ይሁን፤ እኔ እፈውሳቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
መኳንንቱ፣ ሹማምቱ፣ አገረ ገዦቹና የቤተ መንግሥት አማካሪዎችም በዙሪያቸው ተሰበሰቡ፤ እነርሱም እሳቱ ሰውነታቸውን እንዳልጐዳ፣ ከራሳቸውም ጠጕር አንዲቷ እንኳ እንዳልተቃጠለች አዩ፤ የመጐናጸፊያቸው መልክ አልተለወጠም፤ የእሳትም ሽታ በላያቸው አልነበረም።
እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቈርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፣ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ አምላክ መኖሩን ያውቃል።