ከእንግዲህ ሰነፍ ጨዋ አይባልም፤ ጋጠወጥም አይከበርም።
በሰዎች ዘንድ ክፋት ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ፣ ዐመፀኞች በየአቅጣጫው በዛቻ ይዞራሉ።
ነውረኛ በፊቱ የተናቀ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፤ ዋጋ የሚያስከፍለውም ቢሆን፣ ቃለ መሐላውን የሚጠብቅ፤
የጋጠወጥ ዘዴ ክፉ ነው፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆን፣ ድኻን በሐሰት ለማጥፋት፣ ክፋት ያውጠነጥናል።
ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፣ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
በዚያ ጊዜም እንደ ገና በጻድቁና በኀጢአተኛው መካከል፣ እግዚአብሔርን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት ታያላችሁ።
ጌታዬ፣ ያን ምናምንቴ ሰው ናባልን ከቁም ነገር አይቍጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለ ሆነ፣ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም ዐብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጕልማሶች አላየኋቸውም።