ውርደትና ኀፍረት ብቻ እንጂ ርዳታም ሆነ ረብ በማያስገኙላቸው፣ ምንም ጥቅም በማይሰጧቸው ሰዎች ምክንያት ሁሉም ለኀፍረት ይዳረጋሉ።”
በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
ደግሞም ‘አይሆንም፣ በፈረስ እንሸሻለን’ አላችሁ፤ ስለዚህ ትሸሻላችሁ! ደግሞም፣ ‘በፈጣን ፈረስ እናመልጣለን’ አላችሁ፤ ስለዚህ አሳዳጆቻችሁም ፈጣን ይሆናሉ።
ርዳታዋም ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ወደ ሆነው ወደ ግብጽ ይሄዳሉ። ስለዚህ ስሟን፣ ረዓብ፣ ምንም የማትጠቅም ብዬ እጠራታለሁ።
እነሆ፤ እንዲህ የምትመካባት ግብጽ የሚደገፍባትን ሰው እጅ ወግታ የምታቈስል የተቀጠቀጠች ሸንበቆ ናት! የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንም ለሚመኩበት ሁሉ እንደዚሁ ነው።
መንገድሽን እየለዋወጥሽ፣ ለምን ትሮጫለሽ? አሦር እንዳዋረደሽ፣ ግብጽም እንዲሁ ያዋርድሻል።