Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኢሳይያስ 30:16

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም ‘አይሆንም፣ በፈረስ እንሸሻለን’ አላችሁ፤ ስለዚህ ትሸሻላችሁ! ደግሞም፣ ‘በፈጣን ፈረስ እናመልጣለን’ አላችሁ፤ ስለዚህ አሳዳጆቻችሁም ፈጣን ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁን እንጂ የባቢሎናውያንም ሰራዊት ንጉሡን ተከታትሎ በማሳደድ በኢያሪኮ ሜዳ ላይ ደረሱበት። ወታደሮቹም ሁሉ ተለይተውት ተበታትነው ሳለ

ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ?

እርሱ በፈረስ ኀይል አይደሰትም፤ በሯጭም ብርታት ላይ ደስታውን አያደርግም።

በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤ በብርቱ ጕልበቱም ማንንም አያድንም።

ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ሀብታቸውም ልክ የለውም። ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤ የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም።

ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣ ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብጽ ለሚወርዱ፣ በፈረሶች ለሚታመኑ፣ በሠረገሎቻቸው ብዛት፣ በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው!

ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።

የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ እነርሱን ባዩ ጊዜ ሸሹ፤ በሌሊት በንጉሡ አትክልት ስፍራ በኩል አድርገው በሁለቱ ቅጥር መካከል ከከተማዪቱ ወጡ፤ ወደ ዓረባም አመሩ።

እነሆ፤ እንደ ደመና ይንሰራፋል፤ ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣሉ፤ ፈረሶቹም ከንስር ይፈጥናሉ፤ መጥፋታችን ነውና ወዮልን!

“ፈጣኑ መሸሽ አይችልም፤ ብርቱውም አያመልጥም፤ በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ ተሰናክለው ወደቁ።

የከተማዪቱም ቅጥር ተነደለ፤ ሰራዊቱም ሁሉ ኰብልሎ ሄደ። ባቢሎናውያን በከተማዪቱ ዙሪያ ቢኖሩም፣ በንጉሡ የአትክልት ስፍራ አጠገብ በሁለት ቅጥሮች መካከል ባለው በር በሌሊት ከተማዪቱን ጥለው ሸሹ፤ ወደ ዓረባም አመሩ።

ከሰማይ ንስሮች ይልቅ፣ ጠላቶቻችን ፈጣኖች ናቸው፤ በተራሮች ላይ አሳደዱን፤ በምድረ በዳም ሸመቁብን።

ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “መድረኮቹ እንዲናወጡ፣ ጕልላቶቹን ምታ፤ በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤ የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ አንድም ሰው አይሸሽም፤ ቢሸሽም የሚያመልጥ የለም።

እናንተ በለኪሶ የምትኖሩ፣ ፈረሶችን ከሠረገላው ጋራ አያይዙ፤ ለጽዮን ሴት ልጅ፣ የኀጢአት መጀመሪያ እናንተ ነበራችሁ፤ የእስራኤል በደል በእናንተ ዘንድ ተገኝቷልና።

ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው። ፈረሰኞቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ ከሩቅ ስፍራም ይመጣሉ። ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ፤

እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀቂያ ትሆናለህ።

እግዚአብሔር እንደ ንስር ፈጥኖ የሚወርድንና ቋንቋውን የማታውቀውን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፣ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣብሃል፤




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች