ሰውም በአባቱ ቤት ከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፣ “አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ ይህንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ!” ይለዋል።
እርሱ ግን በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እኔ መፍትሒ አልሆንም፤ በቤቴም ልብስና ምግብ የለኝም፤ የሕዝብ መሪ አታድርጉኝ” ይላል።
በዚያ ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፣ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፣ ውርደታችንን አስቀርልን!” ይሉታል።
ኢየሱስም ሰዎቹ መጥተው በግድ ሊያነግሡት እንዳሰቡ ዐውቆ እንደ ገና ብቻውን ወደ ተራራ ገለል አለ።