ስለዚህ፣ ጌታ በጽዮን ሴቶች ዐናት ላይ ቈረቈር ያመጣል፤ እግዚአብሔርም ራሳቸውን ቡሓ ያደርጋል።”
እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት ውጡ፤ ንጉሥ ሰሎሞን አክሊሉን ደፍቶ እዩት፤ ዘውዱም ልቡ ሐሤት ባደረገባት፣ በዚያች በሰርጉ ዕለት፣ እናቱ የደፋችለት ነው።
እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብጻውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብጽን ያዋርዳል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፣ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፣ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።
በዚያም ቀን ጌታ የክብር ጌጣቸውን ይነጥቃቸዋል፤ የእግር አንባሩን፣ የጠጕር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን የዐንገት ጌጥ፣
“ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽ ራስሽን ብትጠይቂ፣ ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣ በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣ ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።
ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቍስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ።
እናንተ በሻፊር የምትኖሩ፣ ዕርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ዕለፉ፤ በጸዓናን የሚኖሩ ከዚያ አይወጡም፤ ቤትዔጼል በሐዘን ላይ ናት፤ ለእናንተም መጠጊያ ልትሆን አትችልም።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ፤ ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልበዋለሁ፤ ዕርቃንሽን ለአሕዛብ፣ ኀፍረትሽንም ለነገሥታት አሳያለሁ።
እግዚአብሔር በማትድንበት በግብጽ ብጉንጅ፣ በዕባጭ፣ በሚመግል ቍስልና በዕከክ ያሠቃይሃል።
የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውን ምልክት በተቀበሉትና ለምስሉም በሰገዱት ሰዎች ላይ ክፉኛ የሚያሠቃይ ቍስል ወጣባቸው።