Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኢሳይያስ 29:22

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው እግዚአብሔር ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፤ “ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም፤ ፊቱም ከእንግዲህ አይለዋወጥም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”

አንተ ትል ያዕቆብ፣ ታናሽ እስራኤል ሆይ፤ ‘አትፍራ እኔ እረዳሃለሁ’ ” ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህ የእስራኤል ቅዱስ ነው።

እስራኤል ግን በእግዚአብሔር፣ በዘላለም ድነት ይድናል፤ እናንተም ለዘላለም፣ አታፍሩም፤ አትዋረዱም።

ነገር ግን የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ሞገስንም ያገኛሉ።

ጌታ እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልዋረድም፤ ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌአለሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።

እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።

ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፣ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሣራ ተመልከቱ፤ በጠራሁት ጊዜ አንድ ራሱን ብቻ ነበር፤ ባረክሁት፤ አበዛሁትም።

“አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤ የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤ የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።

አብርሃም ባያውቀን፣ እስራኤልም ባያስታውሰን እንኳ፣ አንተ እኮ አባታችን ነህ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤ ከጥንትም ቢሆን ስምህ “ቤዛችን” ነው።

“ ‘ስለዚህ፤ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤ እስራኤል ሆይ፤ አትደንግጥ፤’ ይላል እግዚአብሔር። ‘አንተን ከሩቅ አገር፣ ዘርህንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ፤ ያዕቆብ ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፤ የሚያስፈራውም አይኖርም።

“ ‘ባሪያዬ ዳዊት በላያቸው ይነግሣል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል፤ ሕጌን ይከተላሉ፤ ሥርዐቴንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።

መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሚሆንበት ጊዜ፣ አሕዛብ እኔ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ቀደስሁ ያውቃሉ።’ ”

“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ያዕቆብን አሁን ከስደት እመልሰዋለሁ፤ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እራራለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ።

ከዚያም እኔ በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፣ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፣ እንደ እኔም ያለ፣ ሌላ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤም ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም።

“የእስራኤል አምላክ፣ ጌታ ይመስገን፤ መጥቶ ሕዝቡን ተቤዥቷልና።

እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች