እናንተ ነገሮችን ትገለብጣላችሁ ሸክላ ሠሪውን እንደ ሸክላ ትመለከታላችሁ! ለመሆኑ፣ ተሠሪ ሠሪውን፣ “እርሱ አልሠራኝም” ይለዋልን? ሸክላ የሠራውን፣ “እርሱ ምንም አያውቅም” ይለዋልን?
እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ ትቢያ መሆናችንንም ያስባል።
መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው።
እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድርን ባድማ ያደርጋታል፤ ፈጽሞ ያጠፋታል፤ የፍርስራሽ ክምር ያደርጋታል፤ ነዋሪዎቿንም ይበትናል።
ይህም ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ሸክላዎች፣ አንተም ሸክላ ሠሪ ነህ፤ ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን፤
ነገር ግን ሊያገኟቸው አልቻሉም፤ ስለዚህ ኢያሶንንና ሌሎች ወንድሞችን በከተማው ባለሥልጣናት ፊት እየጐተቷቸው እንዲህ እያሉ ጮኹ፤ “እነዚህ ሰዎች ዓለሙን ሁሉ ሲያውኩ ቈይተው፣ አሁን ደግሞ ወደዚህ መጥተዋል፤