የተርሴስ ልጅ ሆይ፤ ከእንግዲህ የሚከለክልሽ የለምና እንደ አባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ።
የተከበሩትን ውርደት ያከናንባል፤ ብርቱዎችንም ትጥቅ ያስፈታል።
ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ እግዚአብሔር ነው።
እንዲሁም በአባይ ዳር፣ በወንዙ መፋሰሻ ላይ ያሉት ተክሎች ይጠወልጋሉ። በአባይ ዳር የተዘራው ዕርሻ ሁሉ፣ በነፋስ ይወሰዳል፤ ምንም አይቀርም።
እግዚአብሔር እጁን በባሕር ላይ ዘረጋ፤ መንግሥታቷንም አስደነገጠ፤ የከነዓንም ምሽጎች እንዲፈርሱ፣ ትእዛዝ ሰጠ፤
እናንተ የተርሴስ መርከቦች፣ ዋይ በሉ፤ ምሽጋችሁ ፈርሷል!
የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣ በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኗል።
የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተለይቷታል፤ መሳፍንቷ፣ መሰማሪያ እንዳጣ ዋሊያ ናቸው፤ በአሳዳጆቻቸው ፊት፣ በድካም ሸሹ።
አሁን በመውደቂያሽ ቀን፣ በጠረፍ ያሉ አገሮች ተናወጡ፤ ከመፍረስሽም የተነሣ፤ በባሕር ውስጥ ያሉ ደሴቶች ተደናገጡ።’
የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የባዕዳንን መንግሥታት ኀይል አጠፋለሁ፤ ሠረገሎችንና ሠረገለኞችን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችና ጋላቢዎቻቸውም በገዛ ወንድሞቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።
ገና ደካሞች ሳለን፣ ልክ ጊዜው ሲደርስ፣ ክርስቶስ ስለ ኀጢአተኞች ሞቷልና።
ሳሙኤል ከተናገረው ቃል የተነሣ፣ ሳኦል በፍርሀት ተውጦ ወዲያውኑ በቁመቱ ሙሉ መሬት ላይ ወደቀ፤ ቀኑንና ሌሊቱን ሁሉ እህል ስላልቀመሰ ጕልበቱ ዝሎ ነበር።