ስለዚህ፣ “ከእኔ ራቁ፤ አምርሬ ላልቅስበት፣ ስለ ሕዝቤ ጥፋት፣ ልታጽናኑኝ አትሞክሩ” አልሁ።
መርዶክዮስ የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ፤ ከዚያም ማቅ ለብሶ፣ በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ አምርሮ እየጮኸ ወደ ከተማዪቱ መካከል ወጣ።
በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ ነፍሴም አልጽናና አለች።
በየመንገዱም ማቅ ይለብሳሉ፤ በየሰገነቱና በየአደባባዩ ሁሉም ያለቅሳሉ፤ እንባም ይራጫሉ።
እነሆ፤ ጐበዞቻቸው በየመንገዱ ይጮኻሉ፤ የሰላም መልእክተኞችም አምርረው ያለቅሳሉ።
ባትሰሙ ግን፣ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኳልና፣ ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤ እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ ከራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፣ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።”
ወይ አበሳዬ! ወይ አበሳዬ! ሥቃይ በሥቃይ ላይ ሆነብኝ፤ አወይ፣ የልቤ ጭንቀት! ልቤ ክፉኛ ይመታል፤ ዝም ማለት አልችልም፤ የመለከትን ድምፅ፣ የጦርነትንም ውካታ ሰምቻለሁና።
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ ምርር ብለሽ አልቅሺ፤ አጥፊው በድንገት፣ በላያችን ይመጣልና።
በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ ልቤ በውስጤ ዝላለች።
ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጕረፊያ በሆኑልኝ!
እነርሱ ፈጥነው ይምጡ፤ ዐይኖቻችን እንባ እስኪያጐርፉ፣ ሽፋሽፍቶቻችንም ውሃ እስኪያመነጩ፣ ስለ እኛ ሙሾ ያውርዱልን።
ዐይኔ በልቅሶ ደከመ፤ ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣ በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤ ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና።
“ ‘በእጁ እንዲያዝ፣ ሰይፉ ሊወለወል ተሰጥቷል፤ ገዳዩ በእጁ እንዲጨብጠው፣ ተስሏል፤ ተወልውሏል።
ስለ አንቺ ጠጕራቸውን ይላጫሉ፤ ማቅም ይለብሳሉ፤ በነፍስ ምሬት፣ በመራራም ሐዘን ያለቅሱልሻል።
በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤ እንደ ጕጕትም አቃስታለሁ።
“የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።”
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ፣ “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ብሎ ኢየሱስ የተናገረው ቃል ትዝ አለው፤ ጴጥሮስም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ።
ይህም ታሪክ ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የነበሩት ያስተላለፉልን ነው።
ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤