የተነደፈ የተልባ እግር የሚፈትሉ፣ የተባዘተ ጥጥ የሚሠሩ ሸማኔዎችም ተስፋ ይቈርጣሉ።
የሰሎሞን ፈረሶች የመጡት ከግብጽና ከቀዌ ሲሆን፣ ከቀዌ የገዟቸውም የንጉሡ ነጋዴዎች ነበሩ።
ሁለቱን አዕማድ፣ በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ሁለት ባለሳሕን ጕልላቶችን፤ በአዕማዱ ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ሁለት ጕልላቶችን ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤
የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤ የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጐሣዎች አባት ለዓዳ፣
ዐልጋዬን ከግብጽ የመጣ፣ ጌጠኛ በፍታ አልብሼዋለሁ።
የመርከቦችሽ ሸራ ጥልፍ ሥራ ያለበት የግብጽ በፍታ ነበረ፤ ይህም እንደ ዐርማ አገለገለሽ። መጋረጃዎችሽ ከኤሊሳ ጠረፍ የመጡ፣ ባለሰማያዊና ሐምራዊ ቀለም ነበሩ።