የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ የመንጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።
ያለ አንዳች ሥጋት ትተኛለህ፤ ብዙ ሰዎችም ደጅ ይጠኑሃል።
የተመሸገባት ከተማ ባዶዋን ቀርታለች፤ እንደ ምድረ በዳም የተተወች ስፍራ ሆናለች፤ ጥጆች በዚያ ይሰማራሉ፤ እዚያም ይተኛሉ፤ ቅርንጫፎቿንም ልጠው ይበላሉ።
በጎችም በገዛ መሰማሪያቸው እንደሚሰማሩ ሆነው ይግጣሉ፤ የበግ ጠቦቶችም በባለጠጎች ፍርስራሽ ላይ ሣር ይበላሉ።
በዚያ ቀን፣ አንድ ሰው አንዲት ጊደርና ሁለት በግ ብቻ ይተርፈዋል።
ከሚሰጡትም የተትረፈረፈ ወተት ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱም የቀሩ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላሉ።
አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።
የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ የሚያባርራቸውም አይኖርም።
የረባት ከተማ የግመሎች መሰማሪያ፣ አሞንንም የበጎች መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
የሚያስፈራቸው ማንም ሳይኖር በምድራቸው ያለ ሥጋት በሚኖሩበት ጊዜ፣ ውርደታቸውንና ለእኔ ባለ መታመን የኖሩበትን ዘመን ይረሳሉ።
እያንዳንዱ ሰው በገዛ ወይኑ ሥር፣ ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፤ የሚያስፈራቸው አይኖርም፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና።
የቀርጤስ ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩ ዳር ያለው ምድር፣ የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤
የጋድ ልጆች፤ ዲቦንን፣ አጣሮትን፣ አሮዔርን፣
በአርኖን ሸለቆ ጫፍ ካለችው ከአሮዔርና በሸለቆው ውስጥ ከምትገኘዋ ከተማ አንሥቶ እስከ ገለዓድ ካሉት ከተሞች አንዳቸውም እንኳ ሊገቱን አልቻሉም። አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን።
በዚያ ጊዜ ከያዝነው ምድር ላይ በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር አንሥቶ በስተሰሜን ያለውን ግዛት፣ በተጨማሪም ኰረብታማውን የገለዓድ አገር እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።
ድንበራቸው ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔርና ከሸለቆው መካከል ካለችው ከተማ አንሥቶ ያለው ግዛት ሲሆን፣ ሜድባ አጠገብ ያለውን ደጋውን አገር በሙሉ፣
ድንበራቸው ኢያዜር፣ የገለዓድን ከተሞች በሙሉ በረባት አጠገብ እስካለው እስከ አሮዔር የሚደርሰውን የአሞናውያን አገር እኩሌታ፣