Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኢሳይያስ 17:14

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ ሲመሽ ድንገተኛ ሽብር ሆነ! ከመንጋቱ በፊት ግን አንዳቸውም አልተገኙም። የዘረፉን ዕድል ፈንታ፣ የበዘበዙን ዕጣ ይህ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፤ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የተግሣጽና የውርደት ቀን ነው፤ ልጆች ሊወለዱ ሲሉ ብርታት እንደሚታጣበት ቀን ሆኗል።

በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።

እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች የወሰነው ዕድል ፈንታ፣ ከአምላክም ዘንድ የተመደበላቸው ቋሚ ቅርስ ይህ ነው።”

ዳግመኛ በዚያ ሳልፍ፣ እነሆ፣ በቦታው አልነበረም፤ ብፈልገውም አልተገኘም።

እግዚአብሔር ይፋረድላቸዋልና፤ የሚቀሟቸውንም ይቀማቸዋል።

በአንተ ላይ ያመጣሁትን ቅጣት በጥቂት ጊዜ ውስጥ አቆማለሁ፤ በእነርሱም ላይ መቅሠፍቴን አመጣለሁ።”

ጠባቂውም መለሰ፤ “ይነጋል፤ ግን ተመልሶ ይመሻል፤ መጠየቅ ከፈለጋችሁ፣ ጠይቁ፤ ነገር ግን ተመልሳችሁ ኑ” አለ።

ነገር ግን አርኤልን እከብባለሁ፤ ታለቅሳለች፤ ዋይ ዋይ ትላለች፤ ለእኔም እንደ መሠዊያ ስፍራ ትሆንልኛለች።

ነገር ግን ብዙ ጠላቶችሽ እንደ ትቢያ ብናኝ፣ የጨካኞች መንጋ በነፋስ እንደሚነዳ ገለባ ይሆናሉ። ድንገት ሳይታሰብም፣

አርኤልን የሚወጋ የአሕዛብ ሁሉ መንጋ፣ በእርሷና በምሽጓ ላይ አደጋ የሚጥልና የሚከብባት፣ እንደ ሕልም በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናል።

እስትንፋሱ እንደሚጠራርግ፣ እስከ ዐንገት እንደሚደርስም የውሃ ሙላት ነው፤ መንግሥታትን በጥፋት ወንፊት ያበጥራቸዋል፤ በሕዝቦችም መንጋጋ፣ መንገድ የሚያስት ልጓም ያስገባል።

አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣ አንት አጥፊ፣ ወዮልህ! አንተ ሳትካድ የምትክድ፣ አንት ከዳተኛ፣ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ፣ ትጠፋለህ፤ ክሕደትህንም በተውህ ጊዜ ትከዳለህ።

የቀደመው መከራ ትዝ እያለህ፣ “ያ ዋና አለቃ የት አለ? ግብር ተቀባዩስ ወዴት ሄደ? የመጠበቂያ ማማ ኀላፊውስ የት አለ?” ትላለህ።

ድርሻ ድርሻቸውን ይመድብላቸዋል፤ እጁም ለክታ ታካፍላቸዋለች። ለዘላለም የእነርሱ ትሆናለች፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ይኖሩባታል።

ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣ አታገኛቸውም፤ የሚዋጉህም፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።

እኔን ረስተሽ፣ በከንቱ አማልክት ስለ ታመንሽ፣ ያወጅሁልሽ ድርሻሽ፣ ዕጣ ፈንታሽ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር፤

እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረች፤ የመከሩም በኵር ነበረች፤ የዋጧት ሁሉ በደለኞች ሆኑ፤ መዓትም ደረሰባቸው’ ” ይላል እግዚአብሔር።

እኔ ግን ዔሳውን አራቍተዋለሁ፤ መደበቅም እንዳይችል፣ መሸሸጊያ ስፍራዎቹን እገልጣለሁ፤ ልጆቹ፣ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ይጠፋሉ፤ እርሱም ራሱ አይኖርም።

ከሜዳ ላይ ዕንጨት መልቀም፣ ከዱርም ዛፍ መቍረጥ አያስፈልጋቸውም፤ የጦር መሣሪያቸውን በመማገድ ይጠቀማሉና። የዘረፏቸውን ይዘርፋሉ፤ የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

እግዚአብሔርም በተቀደሰችው ምድር ይሁዳን ርስቱ አድርጎ ይወርሳል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደ ገና ይመርጣል።

“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤ አንተን የሚወድዱህ ግን፣ የንጋት ፀሓይ በኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።” ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች