ስለዚህ ሞዓባውያን ዋይ ይላሉ፤ በአንድነትም ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማሉ፤ ስለ ቂርሐራሴት ከተማ ሰዎች ትዝታ፣ በሐዘን ያለቅሳሉ።
ከተሞቹን ደመሰሱ፤ መልካሙን የዕርሻ መሬት ሁሉ እስኪሸፍነው ድረስ፣ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ድንጋይ ጣለበት፤ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤ ጥሩ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቈርጠው ጣሉ። ቂርሐራሴት ብቻ ከነድንጋይዋ ቀርታ ነበር፤ እርሷንም ቢሆን ባለወንጭፉ ሰራዊት ከብቦ አደጋ ጣለባት።
እንዲሁም ሩቅ ከሆነው ከይሳኮር፣ ከዛብሎንና ከንፍታሌም አገር ሳይቀር ጎረቤቶቻቸው በአህያ፣ በግመል፣ በበቅሎና በበሬ ጭነው ምግብ አመጡላቸው፤ በእስራኤል ታላቅ ደስታ ስለ ሆነ ዱቄት፣ የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣ የወይን ጠጅ፣ የወይራ ዘይት፣ የቀንድ ከብትና በጎች በገፍ ቀርበው ነበር።
ከዚያም ለእስራኤል ሁሉ ለወንዱም ለሴቱም አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ፣ አንዳንድ ሙዳ ሥጋና አንዳንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ ሰጠ።
ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ እንደ በገና የሐዘን እንጕርጕሮ ታሰማለች፤ አንጀቴም ስለ ቂርሔሬስ ታለቅሳለች፤
ሰዎች፣ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሽኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፣ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?
ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤ የሞዓብን መደምሰስ፣ በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።
ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ ለሞዓብ ምድር ሁሉ ዋይ እላለሁ፤ ለቂርሔሬስ ሰዎችም የልቅሶ ድምፅ አሰማለሁ።