ነገር ግን ወደ ሲኦል፣ ወደ ጥልቁም ጕድጓድ ወርደሃል።
የሚያዩህም አትኵረው እየተመለከቱህ፣ በመገረም ስለ አንተ እንዲህ ይላሉ፤ “ያ ምድርን ያናወጠ፣ መንግሥታትን ያንቀጠቀጠ፣ ይህ ሰው ነውን?
የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤ የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣ የተኵራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።
ስለዚህ በውሃ አጠገብ ያለ ማንኛውም ዛፍ፣ ጫፎቹን ችምችም ካለው ቅጠል በላይ ከፍ በማድረግ፣ ከእንግዲህ ራሱን በትዕቢት አያንጠራራም። ከእንግዲህ ውሃ በሚገባ ያገኘ ማንኛውም ዛፍ ወደዚህ ዐይነቱ ከፍታ አይደርስም። ሁሉም ከምድር በታች ወደ ጕድጓድ ከሚወርድ ሟች ጋራ ዐብሮ እንዲሞት ተወስኖበታልና።
ወደ ጕድጓድ ከሚሄዱት ጋራ ወደ መቃብር ባወረድሁት ጊዜ ሲወድቅ በተሰማው ድምፅ አሕዛብ ደነገጡ። ከዚያም የዔድን ዛፎች ሁሉ፣ ምርጥና ልዩ የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች፣ ውሃ የጠገቡትም ዛፎች ሁሉ ከምድር በታች ሆነው ተጽናኑ።
መቃብራቸው በጥልቁ ጕድጓድ ውስጥ ነው፤ ሰራዊቷም በመቃብሯ ዙሪያ ተረፍርፏል። በሕያዋን ምድር ሽብርን የነዙ ሁሉ ታርደዋል፤ በሰይፍም ወድቀዋል።
አንተ በሰንጣቃ ዐለት ውስጥ የምትኖር፣ መኖሪያህንም በከፍታ ስፍራ ያደረግህ፣ ለራስህም፣ ‘ማን ወደ ምድር ሊያወርደኝ ይችላል?’ የምትል፣ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።
አንቺም ቅፍርናሆም፤ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ልትዪ ነውን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ታምራት በሰዶም ቢደረግ ኖሮ፣ እስከ ዛሬ በቈየች ነበር።
አንቺም ቅፍርናሆም፤ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ ልትዪ ነውን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከርሱም ጋራ በፊቱ ምልክቶችን ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳተ። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ተጣሉ።