Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኢሳይያስ 13:19

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የመንግሥታት ዕንቍ፣ የከለዳውያን ትምክሕት የሆነችውን ባቢሎንን፣ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያቃጥል ዲንና እሳት አዘነበባቸው።

እነዚያንም ከተሞችና ረባዳውን ምድር በሙሉ፣ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ፣ የምድሩን ቡቃያ ሳይቀር ገለባበጠው።

የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ያየው ንግር፤

እነሆ፤ አንድ ሰው በፈረሶች በሚሳብ በሠረገላ መጥቷል፤ እንዲህም ሲል መለሰ፣ ‘ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች! የአማልክቷም ምስሎች ሁሉ፣ ተሰባብረው ምድር ላይ ወደቁ!’ ”

“አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ወደ ጨለማ ግቢ፤ ዝም ብለሽም ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ የመንግሥታት እመቤት ተብለሽ አትጠሪም።

“ሁላችሁም በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አድምጡም፤ ከጣዖቶች አስቀድሞ እነዚህን የተናገረ ማን ነው? የእግዚአብሔር ምርጥ ወዳጅ የሆነ፣ እርሱ በባቢሎን ላይ ያቀደውን እንዲፈጽም ያደርገዋል፤ ክንዱም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።

“ነገር ግን ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ፣ የባቢሎንን ንጉሥና ሕዝቡን፣ የባቢሎናውያንንም ምድር ስለ በደላቸው እቀጣቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለዘላለምም ባድማ አደርጋታለሁ፤

በዙሪያቸው ካሉት ከተሞች ጋራ፣ ሰዶምና ገሞራ እንደ ተገለበጡ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም።

እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን፣ በዙሪያቸውም የነበሩትን ከተሞች ያለ ነዋሪ እንዳስቀረኋቸው” ይላል እግዚአብሔር፤ “እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤ አንድም ሰው አይቀመጥባትም።

ከአንቺ ለማእዘን የሚሆን ድንጋይ፣ ለመሠረትም የሚሆን ዐለት አይወሰድም፤ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ሰው በዚያ መኖር እስከማይችል ድረስ፣ የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ፣ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደው ስለሚጸና፣ ምድር ትናወጣለች፤ በሥቃይም ትወራጫለች።

“ሼሻክ እንዴት ተማረከች! የምድር ሁሉ ትምክሕትስ እንዴት ተያዘች! ባቢሎን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ፣ ምንኛ አስደንጋጭ ሆነች።

እንዲህም በል፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህችን ስፍራ ሰውም ሆነ እንስሳ እስከማይኖርባት ድረስ ለዘላለም ባድማ አደርጋታለሁ ብለሃል።’

“በብርቱ ኀይሌ፣ ለገናናው ክብሬ ንጉሣዊ መኖሪያ ትሆን ዘንድ ያሠራኋት ታላቂቷ ባቢሎን ይህች አይደለችምን?” አለ።

“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣ አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።

ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ሞዓብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያን እንደ ገሞራ፣ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጕድጓድ ለዘላለም ጠፍ ይሆናሉ። ከሕዝቤ የቀሩት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ።”

ይኸውም ቀደም ሲል ኢሳይያስ እንደ ተናገረው ነው፤ “የሰራዊት ጌታ፣ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንን፣ ገሞራንም በመሰልን ነበር።”

ምድሪቱ በሙሉ የተቃጠለ ጨውና ዲን ዐመድ ትሆናለች። አንዳች ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አያቈጠቍጥባትም፤ የሚያድግ ተክል አይገኝባትም። የሚደርስባት ውድመት እግዚአብሔር በታላቅ ቍጣ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፣ እንደ አዳማና ስቦይ ጥፋት ይሆናል።

“ጭነታቸውን ከእንግዲህ የሚገዛ ስለሌለ፣ የምድር ነጋዴዎችም ስለ እርሷ ያለቅሳሉ፤ ያዝናሉ፤

በራሳቸውም ላይ አቧራ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ እንዲህ ብለው ጮኹ፤ “ ‘በባሕር ላይ መርከቦች ያላቸው ሁሉ፣ በርሷም ሀብት የበለጸጉ፣ ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት! በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፍታለች!’




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች